በኢትዮጵያ ከ900 በላይ የምግብ ዘይት አምራቾች ቢኖሩም የገበያ ድርሻቸው ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሀገሪቱ የምግብ ዘይት አምራች ድርጅቶች መካከል በፋብሪካ ደረጃ ያሉት ከ15 እስከ 20 በመቶ ያህሉ ብቻ ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ በውስን ቦታና ጥቂት መጠን የሚያመርቱ ናቸው ተብሏል።

በዘርፉ ላይ አተኩሮ ዛሬ በተካሄደ ውይይት አምራቾቹ እንደገለጹት፥ የቅባት እህሎች ሙሉ በሙሉ ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ መደረጉና ደላሎች በቅባት እህሎች ገበያ ሰንሰላት ላይ እንዲገቡ መደረጉ ጥሬ እቃዎችን እንዳያገኙና በሙሉ አቅም እንዳያመርቱ አድርጓል።

ከውጭ የሚገቡ የምግብ ዘይቶች ከቀረጥ ነጻ ሲሆኑ፥ የሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲቀረጡ መደረጉ ለዘርፉ ውጤታማነት መዳከም በምክንያትነት የሚጠቅሱት አምራቾቹ፥ የሀገሪቱን የምግብ ዘይት ቴክኖሎጂና አቅም ያላገናዘበ ደረጃ በመቀመጡም በየጊዜው ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው መሆኑን ነው የተናገሩት።

ይህም የሀገር ውስጥ አምራቹ ለዘርፉ ያለው ድርሻ ከ10 በመቶ በታች እንዲሆን እንዳደረገው እና ሀገሪቱ በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠር ብር ወጪ በማድረግ የምግብ ዘይት ከውጭ እንድታስገባ አድርጓታል ተብሏል።

በመሆኑም በባለፈው ዓመት ብቻ የምግብ ዘይት ከውጭ ለማስገባት 13 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።

 

Share.

About Author

Leave A Reply