በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ አንድ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈ በኋላ መነሳቱ ተገለፀ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሟች አቶ ሂርጳ ነገሮ ለረጅም ጊዜ በፅኑ ህመም ሲሰቃይ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ማለትም ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ህመሙ ፀንቶበት ህይወቱ ያልፋል።

በአካባቢው ባህል መሰረትም ሳይገነዝ ለ1 ሰዓት አከባቢ ከቆየ በኋላ አስከሬኑ ተገንዞ ወደ ተዘጋጀለት ሳጥን ይገባል።

የቀብር ስነ ስርዓቱን ለመፈፀምም ቤተሰቦቹ ሩቅ ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መልዕክት ይልካሉ።

በመቀጠልም ወዳጅ ዘመዶቹ ቦታው እስኪደርሱ ቤተሰቦቹ የተለያዩ የሀዘን ስነ ስርዓቶችን እያከናወኑ ቆይታ አድርገዋል።

ሥርዓቱ እየተከናወነ አስከሬኑ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በግምት ከ5 ሰዓት በላይ ከቆየ በኃላ ግን አንድ አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ።

ግብዓተ መሬቱ ሊፈፀም ስዓታት የቀሩት ሟች ከአስከሬን ሳጥኑ ወስጥ ድምፅ ማሰማት መጀመሩ ተነግሯል፡፡ (ፋና)

Share.

About Author

Leave A Reply