በከፋ ዞን ዋና ከተማ ቦንጋ በደቡብ ልዩ ሀይልና በወጣቶች መካከል ውጥረት ነግሷል። ህዝቡ የዞኑን ባለስልጣናት ስልጣን ልቀቁ እያለ ነው::

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የከፋ ዞን ባለ ስልጣናት ዛሬ ረፋድ ላይ የቦንጋ ከተማ ወጣቶችን ለመሰብሰብ ሞክረው የነበረ ሲሆን ወጣቶቹ ግን በተቃውሞ

መድረኩን በመንጠቅ የካቢኔ  “ስልጣን ልቀቁ” በማለት መድረኩን መንጠቃቸውን ለቃሊቲ ፕሬስ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ወጣቶቹ “ካፋ ላይ ያላችሁ የካቢኔ አባላት የዶክተር አብይን አዲስ አመራር አትደግፉም፣ የነበረውን የድሮ አስተሰባችሁን ልታሸክሙን ትፈልጋላችሁ” በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸው ተነግሯል።

ስብሰባው በከተማው ትልቁ የሸተራሻ ገሮ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን አፍታም ሳይቆይ ተቊርጧል።

ከትላንት ወዲያ የሀገር ሽማግሌዎችን ትላንት የመንግስት ሰራተኞችን ሰብስበው ነበር።

የትላንቱ ስብሰባ  በካፋ ባህል አዳራሽ ሲካሄድ የተነሱ ጥያቄዎች

  1. በግሪን ኮፊ የተባለው ድርጅት የቦታ ይዞታ እና ሃሽሽ በድብቅ እንደሚያመርት
  2. በውሽውሽ እና በጎጀብ እርሻ ልማት ላይ ዞኑ እና አካባቢው ምን እንደተጠቀመ
  3. የክልል ጥያቄ
  4. የመልካም አስተዳደር ችግር
  5. ጠ/ሚ አብይን ስለማትደግፋ ስልጣን ልቀቁ እና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተዋል።                                                                                                                               

Share.

About Author

Leave A Reply