በኬኒያ የሰው ስጋ በምግብነት ሲሸጥ የነበረ ሆቴል ተደረሰበት።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በኬኒያ ናይሮቢ የሰው ስጋ ለምግብነት ሲያቀርብ የነበረ አንድ ሆቴል መዘጋቱ ተነገረ። ሆቴሉ የሚገኝበት አካባቢ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ኢስሊ በመባል የሚታወቀው ስፍራ ነው።

ፖሊስ እንደ ተናገረው በአካባቢው ህዝብ ጥቆማ ወደ ሬስቶራንቱ ሲያመራ የሰው ስጋ እና በላስቲክ የታሸገ የሰው ደም ማግኘቱን አረጋግጧል።

በድርጊቱ የተሳተፉ ስድስት ሴቶችና አራት ወንድ የሆቴሉ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በተደረገው ፍተሻም የጦር መሳሪያዎችና በርካታ ቁጥር ያላቸው የእጅ ስልኮችን ማግኘቱን ፖሊስ አስታውቋል። ~ ቃሊቲ ፕሬስ

ምንጭ – K24

Share.

About Author

Leave A Reply