በወላይታ ሶዶ ከተማ በግለሰብ ቤት የተከማቸ 24 ሺህ ሊትር ቤንዚን ተያዘ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሶዶ መጋቢት 5/2011 በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በህገወጥ መንገድ የተከማቸ 24 ሺህ ሊትር ቤንዚን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

በአስተዳደሩ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አለማየሁ ቶማ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ቤንዚኑ የተያዘው በከተማው የሕብረት ቀበሌ ነዋሪ በሆነ አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ትላንት ጧት 2 ሰዓት ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ቤንዚኑ መያዙን ተናግረዋል።

ለጊዜው ከአካባቢው የተሰወረውን የቤቱን ባለቤት ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ ለማቅረብ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል

Share.

About Author

Leave A Reply