Thursday, January 17

በወልቂጤ ከተማና ዙሪያው ዛሬ ረፋድ ላይ የተቀሰቀሰው ሁከትና ግጭት ተባብሷል።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በወልቂጤ ከተማና ዙሪያዋ በሚኖሩ የጉራጌና ቀቤና ተወላጆች መካከል ለተፈጠረው ግጭት መነሻ ምክንያቱ ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር የተያያዘ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ የደቡብ ክልል ክለቦች ሻምፒዎና በአላባ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ነገር ግን፣ በመጨረሻ ሰዓት የዝግጅቱ ቦታ ከአላባ ወደ ወልቂጤ ከተማ ይቀየራል። በዚህ ሻምፒዎና የወልቂጤ ከተማ እና የቀቤና ወረዳ ይሳተፋሉ።

ከዚህ ቀደም አብዛኞቹ የቀቤና ወረዳ ተጨዋቾች የወልቂጤ ከተማ ተወላጆች የነበሩ ሲሆን በዚህ አመት ግን እነዚህ ተጨዋቾች ለወረዳው ለመጫወት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በትላንትናው ዕለት በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው የእርግ ኳስ ጨዋታ የቀቤና ወረዳ ይሸነፋል።

በጨዋታው የቀቤና ወረዳ የተሸነፈው የወልቂጤ ከተማ ተወላጆች የሆኑ ተጨዋቾች ለወረዳው ለመጫወት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ በመጥቀስ የተወሰኑ የቀቤና ደጋፊዎች ከወልቂጤ ደጋፊዎች ጋር ግጭት ውስጥ ይገባሉ። ትላንት በዚህ መልኩ የተቀሰቀሰው ግጭት እየከረረ ሄዶ ዛሬ ላይ ወደ ብሔር ግጭት ተቀይሯል።

በእርግጥ የወልቂጤ መሃል ከተማ ሰላማዊ ሲሆን ነዋሪዎችም የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴያቸውን በማድረግ ላይ ናቸው። በከተማው መግቢያና መውጫ፣ በአጠቃላይ በወልቂጤ ከተማ ዙሪያ ያለው ሁኔታ ግን ከመሃል ከተማው ፍፁም የተለየ ነው። ምክንያቱም የቀቤና ማህብረሰብ የሚኖረው በወልቂጤ ከተማ ዙሪያ ነው። ግጭትና ሁከት የተቀሰቀሰው የሁለቱ ብሔር ተወላጆች በቀጥታ በሚገናኙበት የከተማዋ ዙሪያ ነው።

አሁን ወደ ወልቂጤ ስልክ ደውዬ እንዳረጋገጥኩት በወልቂጤ ከተማ ዙሪያ መኖሪያ ቤቶችና መኪኖች እሳት እየተቃጠሉ ነው። ያነጋገርኳቸው ሰዎች ግጭትና ሁከቱ ከዞኑ የፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ ሊሆን እንደሚገኝ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply