በዓለም ዋንጫ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ሲካሄዱ፤ ስፔክ ከፖርቹጋል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በትናንትናው እለት በይፋ የተከፈተው የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ በዛሬው እለትም ቀጥሎ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በዛሬው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች ውስጥ በምድብ አንድ ውስጥ የሚገኙት የግብፅ እና የኡራጓይ ጨዋታ አንዱ ነው።

ዛሬ በሴንተራል ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት በሚካሄደው ጨዋታ ላይም የግብፅ ብሄራዊ ቡድን እና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሞሀመድ ሳላህ እንደሚሳተፍ መገለፁን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የግብፅ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሄድተር ኩፐር፥ ሞሀመድ ሳላህ በዛሬው ጨዋታ ላይ ተሰልፎ እንደሚጫወት መቶ በመቶ ላረጋግጥላችሁ እችላለው ብለዋል።

የ25 ዓመቱ ግብፃዊ ሞሃመድ ሳላህ ባሳለፍነው ግንቦት 18 በተካሄደው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የትክሻ ጉዳት ከደረሰበት ወዲህ ተጫውቶ አያውቅም ነበር።

አሰልጣኝ ሄድተር ኩፐር በትናንትናው እለት ግን ሳላህ ለሀገሩ እንደሚጫወት ያረጋገጡ ሲሆን፥ በዓለም ዋንጫው ላይ ከፍተኛ ግብ አግቢ ሊሆን ይችላል የሚል ግምታቸውንም አስቀምጠዋል።

ኡራጓይ በበኩሏ የአማኳይ ስፍራዋ ወጣት ጫዋቾቿን ልታሰልፍ ትችላለች የተባለ ሲሆን፥ የ20 ዓመቱ ሮድሪጉ ቤንታኩር እና የ22 ዓመቱ ናሂታን ናንዴዝ ከእነዚህ ተጠቃሽ ናቸው።

ለኡራጓይ በመሰለፍ ልምድ ያካበቱት ሊዊስ ሱዋሬዝ እና ኤዲሰን ካቫኒ ደግሞ የኡራጓይን ብሄራዊ ቡድን የፊት መስመር እንደሚመሩም ተነግሯል።

በምድብ አንድ ውስጥ የሚገኙት ሩሲያ እና ሳኡዲ አረቢያ ጨዋታቸውን በትናንትናው እለት ያካሄዱ ሲሆን፥ ጨዋታውም በሩሲያ 5ለ0 አሸናፊነት ነው የተጠናቀቀው።

በምድብ ሁለት የተደለደሉት ሀገራትም በዛሬው እለት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

በዚህም መሰረት ዛሬ 12 ሰዓት ላይ ሞሮኮ እና ኢራንን የሚያገናኘው ጨዋታ በቅዱስ ፒተርስበርግ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

ሞሮኮ እና ኢራን በዓለም ዋንጫ መድረክ ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያቸው እንደሆነ ነው የተነገረው።

በምድብ ሁለት ከሚደረጉ ጨዋታዎች ውስጥ ሌላኛው የሆነው እና ፖርቹጋልን ከስፔን የሚያገናኘው ጨዋታም በዓለም ዋንጫው ከሚጠበቁ ጨዋታዎች ውስጥ አንዱ ነው።

የፖርቹጋል እና ስፔን ጨዋታም በዛሬው እለት ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በፊሽት ኦሊምፒክ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

በፖርቹጋል በሄራዊ ቡድን በኩል ምንም ጉዳት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን፥ ሆኖም ግን በቡድኑ አሰላለፍ ምን ሊመስል ይችላል የሚለው እስካሁን ግልፅ አልሆነም።

የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድኖቹ ጆሴ ፎንቴ እና ቡርኖ አልቬስ ከፔፔ ጋር እንደሚጣመሩ የሚጠበቅ ሲሆን፥ አንድሬ ሲልቫ ወይም ጎንካሎ ጉዴስ በአጥቂ መስመር ላይ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ሊጣመሩ ይችላሉ ተብሏል።

አሰልጣኟን በቀየረችው የስፔን ብሄራዊ ቡድን በኩል ደግሞ ዳኒኤል ካቫራል በጡንቻ መሸማቀቅ ምክንያት ከሜዳ ርቆ የቆየ ቢሆንም ከቡድኑ ጋር ተመልሶ ልምምድ ሰርቷል፤ ሆኖም ግን የመሰለፉ ነገር አሁንም አጠራጣሪ ነው።

ስፔን እና ፖርቹዳል በተለያዩ የውድድር መድረኮች ላይ 35 ጊዜ ተገናኝተው የተፋለሙ ሲሆን፥ ስፔን 16 ጊዜ፣ ፖርቾጋል ደግሞ 6 ጊዜ ተሸናንፈው፤ 13 ጊዜ አቻ ተለያይተዋል።

ሁለቱ ሀገራት በዓለም ዋንጫ መድረክ አንድ ጊዜ ብቻ የተገናኙ ሲሆን፥ እሱም የ2010 የዓለም ዋንጫ ነው፤ ጨዋታውም በስፔን 1ለ0 አሸናፊነት ነበር የተጠናቀቀው።

Share.

About Author

Leave A Reply