በደራሽ ጎርፍ ተውጠው የነበሩት የቼራሊያ ሰራተኞች ጉዳት ሳይደርስባቸው ወጡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አቃቂ ክፍለ ከተማ አቃቂ መሿለኪያ ድልዲይ በደራሽ ጎርፍ መሞላቱን ተከትሎ የቼራሊያ የሰራተኞች ሰርቪስ በደራሽ ጎርፍ ተዋጠ።

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የኮሙኒዩኒኬሽን ጉዳዮች የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሽ ተስፋዬ የሰራተኞች ሰርቪስ ሰራተኞቹን እንደጫነ በውሃ መሸፈኑን ገልፀዋል።

የባለስልጣኑ ጠላቂ የነፍስ አድን ባለሙያዎች በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስ የጠለቁትን ሰዎች ማውጣታቸውን አስታውቀዋል።

እንዲሁም በደራሽ ጎርፍ ተውጦ የነበረው ሰርቪስ መውጣቱን ባለሙያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፁ ቢሆንም በክሬን መበጠስ ምክንያት በአሁን ወቅት ለመውጣት አዳጋች ሆኖ በዋልያ ክሬን ሙከራ እየተደረገ ነው።

 

Share.

About Author

Leave A Reply