በደቡብ አፍሪካ የቁም እስረኛ የሆኑት ሬክ ማቻር ወደ አዲስ አበባ ሊዛወሩ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ሀይል መሪ የሆኑት ሬክ ማቻር በቀጣዩ ሀምሌ ወር ላይ ወደ አዲስ አበባ እንደሚዛወሩ ተዘገበ።

ከሱዳን በመገንጠል ራሷን በቻለች ብዙም ሳትቆይ ወደ ጦርነት በመግባት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎቿን ለሞትና ለስደት ያበቃችው ደቡብ ሱዳን ለበርካታ ጊዜያት የሰላምና የእርቅ ውይይቶች በኢትዮጵያ ቢካሄድም እስካሁን ለፍሬ ሊበቃ አልቻለም።

የዚሁ ሂደት ተሳታፊ የነበሩት የተቃውሞ ጎራው መሪ ሬክ ማቻር ከአንድ አመት በፊት በደቡብ አፍሪካ ለህክምና በሄዱበት የቁም እስረኛ መሆናቸው ይታወቃል።

ይሁንና በትናንትናው እለት በፕሪቶሪያ የጎበኟቸው የቀድሞው የኬኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ለሰላማዊ ውይይቱ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ መረዳታቸውን ለመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply