በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተወረወረ የእጅ ቦምብ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ማታ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተወረወረ የእጅ ቦምብ በዘጠኝ ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገለፁ ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ቃልኪዳን ነጋሽ ለኢዜአ እንደገለፁት ከትላንት በስቲያ ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ በዩኒቨርሲቲው ኦዳያአ ግቢ በሚገኝ የማህበራዊ ሳይንስ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ቦምብ ተመርውሯል፡፡

ዶክተር ቃልኪዳን እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት ከተጎጂዎች መካከል አንዱ በዲላ ዩኒቨርቲ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ሲሆን ቀሪዎቹ ህክምናቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል ፡፡

“በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት የለም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ በህክምና ላይ የሚገኘው ተማሪም ያለበት ሁኔታ አስጊ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ጉዳት ያደረሰውን ግለሰብ ለመያዝ ከህግ አስከባሪዎች ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply