በዳሎቻ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መሰንጠቅ 200 ሰዎች ተፈናቀሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አበስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መሰንጠቅ 200 ሰዎች መፈናቀላቸውን የዞኑ አስተዳደር ገለፀ፡፡

የዞኑ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልጀባር አብደላ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፥ በወረዳው የተከሰተው አደጋ ነዋሪዎቹን ከመኖሪያቸው አፈናቅሏል፡፡

ክስተቱ በግምት ርዝመቱ ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ ስፋቱ ደግሞ ሁለት ሜትር የሆነ መሰንጠቅ እንዳስከተለ ገልጸዋል፡፡

የዞኑ አደጋ ስጋት አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ወሲላ አሰፋ በበኩላቸው በሰው ሕይወት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ነዋሪዎቹ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

አደጋውንና ተፈናቃዮቹን በሚመለከት የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ጥናት ይደረጋልም ነው ያሉት።

በአካባቢው የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እሳተ ገሞራ ጋር በተያያዘ የመሬት መሰንጠቅ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል አመላካች ጥናቶች መኖራቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ)

Share.

About Author

Leave A Reply