በጫት ምርትና ሱስ እየናወዘች ያለችው ባህርዳር ከተማ በጫት ንግድ ላይ ቀረጥ ልትጥል ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በጫት ምርትና ሱስ እየናወዘች ያለችው ባህርዳር በጫት ንግድ ላይ ቀረጥ ልትጥል ነው

በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በጫት ምርት ላይ ከነገ ሚያዚያ 17/2010ዓ.ም ጀምሮ ቀረጥ ሊጣል መሆኑ ተገለፀ፡፡

ባሕር ዳር፡ሚያዝያ 16/2010 ዓ/ም(አብመድ)የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ በጫት ምርት ላይ ከነገ ጀምሮ በተደራጁ ማህበራት አማካኝነት የቀረጥ ስራ ይጀመራል፡፡

በዋናነት ቀረጥ ማስቀመጥ ያስፈለገበትን ምክንያትም ሲገልፁ፤ በጫት ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የገዥን አቅም ማዳከምና ጫት የሚቅም ወጣትን ለመታደግ የታሰበ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩልም ለከተማው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ በቅርቡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ወደ ባህር ዳር ከተማ በቀን ብቻ ከ5ሺህ ኪ.ግ በላይ የጫት ምርት ይገባል፡፡

በዚህ መሰረት ለባህር ዳር አካባቢ ከ1 ኪ.ግ ጫት ላይ 5 ብር ቀረጥ የተቀመጠ ሲሆን ከባህር ዳር ውጭ በሚጫኑ የጫት ምርቶች ላይ ከ1 ኪ.ግ የጫት ምርት ላይ 30 ብር የተቀመጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አማራ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ

Share.

About Author

Leave A Reply