በፓርኩ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ለማስመጣት ሀሳብ ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬንያ ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጉዳዩን ለማስፈፀም እየተሰራ መሆኑን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የውጭና ዓለማቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በተለይም ለአብመድ ተናግረዋል።

ኬንያ ፈቃደኛ መሆኗንና የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሩን በቶሎ ለማስመጣትና ቃጠሎውን ለመቆጣጠርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከኬንያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም አቶ ገዛኸኝ ነግረውናል። ሁሉም ፓርኩን በማዳኑ ስራ እንዲረባረብም ጠይቀዋል።

የኢፌዴሪ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ የቱሪስት አስጎብኝ ድርጅቶች እና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፓርኩ ስለተጋረጠበት አደጋ አሁን አዲስ አበባ ላይ እየመከሩ ነው።

ከውይይቱ በኋላም በተቀናጀ መልኩ እሳቱን ለማጥፋት በሚያግዝ ኃላፊነት አደጋው ወደ ተከሰተበት ቦታ እንደሚሄዱ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ አሁንም እየተቃጠለ፤ ብዝሀ ሕይዎቱም ለአደጋ እየተጋለጠ ነው።

ፓርኩ ከ21 ዓመታት ለአደጋ የተጋለጡ የጎብኝ መዳረሻ ስፍራዎች መዝገብ ውሰጥ ቆይታ በኋላ “ከአደጋ ነፃ” ከተባለ ሁለት ዓመታት ሆኖታል። አሁን ደግሞ ተደጋጋሚ ቃጠሎ እየደረሠሰበት ይገኛል። ከሳምንት በፊት በተከሰተው እሳት ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

Share.

About Author

Leave A Reply