Thursday, January 17

“በ2009 በጀት የኦዲት ክትትል ከ173 ተቋማት 148ቱ የኦዲት ጉድለት አለባቸው” የንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በ2009 በጀት የኦዲት ክትትል ከተደረገባቸው 173 ተቋማት 25ቱ ብቻ የኦዲት ግኝት የለሌለባቸው መሆኑ ተገለጸ።

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የኢንስፔክሽን ዳይረክተር አቶ ፈቃዱ አጎናፍር የገንዘብ ጉድለት የታየባቸው ተቋማት ወደ ፊት በህግ አግባብ የሚጠየቁና በግለሰቦች ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር በሀገሪቱ የገንዘብ አስተዳደር ና ግዢ ስርአት ዙርያ ከውስጥ ኦዲተሮች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

በምክክር መድረኩ የውስጥ ኦዲተሮች እርስ በእርስ ያለመስማማት፣ የሙያ ነፃነትን ያለአግባብ መጠቀም፣ የኦዲት ግኝቶችን በወቅቱ ያለማሳወቅና የመንግስት ግዥና ፋይናንስ መመሪያዎችን በትክክል የማወቅ ክፍተቶች እንዳሉባቸው ተመላክቷል።

በ112 ተቋማት የ2009 በጀት ላይ በተደረገ ክትትል ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የአላቂ እቃ ግዥ የተፈጸመ ና በ120 ተቋማት ደግሞ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በአላቂ ንብረቶች ፈሰስ እንካተት ተደርጓል ተብሏል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply