በ340 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባውን የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። ጠ/ሚ አብይ ተገኝተዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል ምረቃ ላት በዛሬው እለት ታድመዋል።

በ340 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባውን የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል ዛሬ ተመርቋል።

በምረቃው ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦመር ሀሰን አልበሽር፣ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ፣ የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፈቂ ማሃማት ተግኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በምረቃው ላይ፥ ጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል በማስገንባቷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ማእከሉ ለጅቡቲ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሀገራትም የጋራ ሀብት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያ ማእከሉ እንደራሷ ፕሮጀክት ትቆጥራለች ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በበኩላቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ ፕሮጀክቱ ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እምነት አለኝ ብለዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply