ባለስልጣኑ ፍቃድ ሳይኖራቸው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ፍቃድ ሳይኖራቸው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የአዲስአበባ ትራንስፖርት ባለስለጣን አሳሰበ።

ባለስልጣኑ በሰጠው መግለጫ ከፍቃድና እውቅና ውጪ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ወደ ህጋዊ ስርአት ሊገቡ እንደሚገባ ገልጿል።

ስራ አስኪያጁ ኢንጂነር ዳዊት ዘለቀ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰራሩን የጣሱ እንቅስቃሴዎች መበራከታቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ አቅራቢ ነን ብለው እየሰሩ የሚገኙ ተቋማት ከባለስለጣኑ ፍቃድ ውጪ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፥ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም ነው ባለስልጣኑ ያሳሰበው።

ባለስልጣኑ ያሉበትን የዘመናዊ አሰራር ክፍተቶች ለማስተካከል እየሰራ እንደሆነም ኢንጅነር ዳዊት ዘለቀ አስታውቋል። ~ ፋና

Share.

About Author

Leave A Reply