ባራክ ኦባማ ዛሬ ለአፍሪካውያን በማንዴላ ልደት ላይ ያስተላለፉት መልእክት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኔልሰን ማንዴላን 100ኛ ዓመት የልደት በዓል መታሰቢያ ላይ በጆሃንስበርግ ለታደሙ 15 ሺህ ሰዎች ካነሷቸው አምስት ነጥቦች መካከልም

1 እውነታዎችን በመቀበል ራስን ለትብብር ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

“ለመተባበር ካሰብን ሀቆችን መቀበል ያስፈልጋል ያ ካልሆነ ግን የተቀመጡበትን መድረክ እያሳዩ እኔ መድረክ ነው ስላችሁ እናንተ አይ ዝሆን ነው የምትሉ ከሆነ መግባባትም መተባበርም አንችም ” ነው ያሉት ኦባማ።

2 ስደተኞችን ጨምሮ የማህብረሰብ እኩልነት መገንባት አለብን።

ስደተኞችን ጨምሮ ሁሉም ማህበረሰብ ያለውን ተሰጥኦና ሃይል ለስኬት እንዲያውለው እኩልነቱ ሊከበርለት ይገባል፤ ተመልከቱ የፈረንሳይን ቡድን መመልከት በቂ ነው ፈረንሳያዊ በመሆናቸው የዓለም ዋንጫን አነሱ ሲሉም ተደምጠዋል።

3 በቢዝነስም ይሁን በፖለቲካው መስክ ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ከህብረተሰቡ ህይወት የተነጠለ ስራ መስራት አክሳሪ እንጅ አትራፊ አይደለም ብለዋል።

4 ዴሞክራሲ ለዘለዓለም ይኑር ሲሉም ተደምጠዋል።

ዴሞክራሲ ከባድ ነገር ቢሆንም እሱን ለመገንባት ከላይ ያሉትን የቅንጦት ጉዳዮች ትተን ከታች ባሉት የዓለም መሰረቶች ላይ እናተኩር ብለዋል።

5 ተስፋ መቁረጥ አይገባም

ኦባማ እንዲህ አሉ “ሃሳባችሁን፣ አቋማችሁን፣ ገንቢ ሚናችሁን እና ድምፃቸሁን ከፍ አድርጎ የማሰማት ሂደታችሁን በፍፁም ማስቆም የለባችሁም፤ ሁሉም ትውልድ ዓለምን እነደገና የመስራት እድል አለው”

የአንድ ሰው ጥንካሬ ብቻውነ ስኬት አይሆንም፤ የጋራ ጥረት ነው ህልማችንን እውን የሚያደርገው ሲሉም ተናግረዋል።

ኦባማ በአንድ ወቅት ኔልሰን ማንዴላ ‘ወጣቶች የጭቆናን ማማ ንደው፤ የነፃነትን ከፍ የማድረግ አቅም አላቸው’ ያሉትን ሀሳብ በመጥቀስ ሌሎች መልካም ነገሮችን ለመተግበር ምቹ ጊዜ ላይ ነን ብለዋል።

ምንጭ  ቢቢሲ

Share.

About Author

Leave A Reply