ብሪታኒያ ፌስ ቡክን 500 ሺህ ፓውንድ ልትቀጣ ነው::

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሐምሌ 04፣2010

ብሪታኒያ ፌስቡክ የደንበኞቹን መረጃ በህገወጥ መንገድ ለሶስተኛ ወገን አስተላልፎ ሰጥቷል በሚል 500 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ልትጥልበት ነው፡፡

በአለማችን ብዙ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ማህበራዊ ሚዲያው ካምብሪጅ አናለቲካ ለተሰኘ የፖለቲካ አማካሪ ኩባንያ ያለ ደንበኞቹ ፍቃድ መረጃዎችን አስተላልፈሃል በሚል ከዚህ በፊት ተከሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም ኩባንያውን ጨምሮ ፌስቡክ በተለይ በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ እንዲሁም በአውሮፓ ህብረት ተከሰው ነበር፡፡

አሁን ላይ ደግሞ የብሪታኒያ የመረጃ ኮሚሽነር ፌስቡክ ካምብሪጅ አናለቲካ ኩባንያ ከደንበኞቹ የወሰደው መረጃ እንዲሰረዝ ባለማድረጉ 500 ሺህ ፓውንድ ቅጣት እንዲጣልበት ጠይቋል፡፡

በአውሮፓዊያኑ 2017 ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን መረጃ ያለአግባብ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የአውሮፓ ህብረት ማህበራዊ ሚዲያው ላይ 95 ሚሊዮን ፓውንድ ቅጣት ጥሎበት እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ፌስቡክ የደንበኞቹን መረጃ አያያዝ አስመልክቶ ህገ መጣሱን ይፋ ያደረገው ካምብሪጅ አናለቲካ በሚባል ኩባንያ ውስጥ ይሰራ የነበረ ክርስቶፈር ዊሊ የተባ ግለሰብ አማካኝነት እንደሆነ ተወስቷል፡፡

በዚህም ካምብሪጅ አናለቲካ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ በህገ ወጥ መንገድ በመጠቀም በአለም በሚካሄዱ የሀገሮች ምርጫ ወቅት ፖለቲከኞች መረጃዎቹን ተጠቅመው በምርጫው እንዲያሸንፉ የሰፋ እንዲል እንዲያገኙ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ካምብሪጅ አናላቲካ በአውሮፓዊያኑ 2016 የአሜሪካው የፕሬዝዳንት ምርጫ ተፎካካሪ ለነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ይሰራ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share.

About Author

Leave A Reply