ብርሀነ ንጉሴ በድምጺ ወያነ ቴሊቪዥን በትግርኛ ቋንቋ የሚተላለፍ ፕሮግራም ማቅረብ ጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ብርሀነ ንጉሴ በድምጺ ወያነ ቴሊቪዥን በትግርኛ ቋንቋ የሚተላለፍ ፕሮግራም ማቅረብ ጀመረ

በተለያዩ ሚዲያዎች በመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢነቱ የሚታወቀው ብርሀነ ንጉሴ የህወሀት ልሳን በሆነው ድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን ላይ ፕሮግራም ማቅረብ መጀመሩን ገልጿል።

ብርሀነ ንጉሴ በኢንስታግራም ባስተላለፈው መረጃ ፕሮግራሙ በትግርኛ ቋንቋ እንደሚቀርብ ገልጿል። ይሁን እንጂ የፕሮግራሙ ይዘትና የምልከታ አድማሱ ሀገራዊ ይሁን ወይም ክልላዊ መሆኑን አልገለጸም።

ብርሀነ ንጉሴ ዛሚ ራዲዮ ከመንግስት አካላት ሲደረግለት የነበረው ድጋፍ ከተቋረጠ በኋላ “ኢትዮፒካ ሊንክ” የተሰኘውን የመዝናኛ ፕሮግራሙን ወደ ፋና ራዲዮ ይዞ የተመለሰ ሲሆን እሱም ራሱ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም ከዳር ደርሶ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

 

 

Share.

About Author

Leave A Reply