ብርቱካን ሚደቅሳ በነገው ዕለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ይሾማሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ነገ ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን በሚያካሂድበት ሥነሥርዓት ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን እንደሚመርጥ ተሰማ፡፡

ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ ከዩናትድ ስቴትስ አሜሪካ ተጠርተው የመጡት የቀድሞ የአንድነት፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲና ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በአሁን ሰዓት በሥራ ላይ የሚገኙትን ወ/ሮ ሳሚያ ዘካርያ ተክተው የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው እንደሚሾሙ ጠቁመዋል፡፡

ቦርዱ ለቀጣይ ምርጫ ራሱን በአዲስ መልክ አደራጅቶ ስሙንም ወደኮምሽንነት ቀይሮ እንደሚመጣና ወ/ት ብርቱካን ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተገምቷል፡፡

በተጨማሪም ምክርቤቱ በነገው ስብሰባው የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መናብርት ሹመት ለማፅደቅ የሚቀርብለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃል፡፡

በዚህ መሠረት በቅርቡ ሹመታቸውን ፓርላማው ውድቅ ባደረጋቸው አመራሮች ምትክ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply