Thursday, January 17

ብአዴንና ኦህዴድ ተቋማቱን ወደ ግል ለማዞር የተስማሙበትን ዝርዝር ሊያሳዉቁን ይገባል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ህወሃት በኢትዮጵያ አይደለም በምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ hegemony ለመፍጠር ያሰበ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ያለዉን የባድመ ጉዳይ ከረዥም ጊዜ የኢኮኖሚ ጥቅም አንጻር አስልቶ ለኤርትራ ዉሰጅልኝ ብሏል፡፡ ይህ የፖለቲካ ሽንፈት ገና ብዙ ጣጣ ያመጣል፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ እንደ አግሬሰር ተቆጠራ ጦርነቱን የጀመረችዉ ኢትዮጵያ ነች በማለት ኤርትራ ካሳ ሁሉ የመጠየቅ መብት ይኖራታል፡፡ በርግጥ ጦርነቱ የጂኦግራፊ ብቻ እንዳልነበር ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡ ዉስብስብ የፖለቲካና፤ማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች እንዳሉበት ተወርቷል፡፡ ባድሜን በመስጠት በቀላሉ ነገሮች የሚዳፈኑ አይደሉም፡፡ ከዛም በላይ በኤርትራና በትግራይ ህዝብ መካከል ያለዉ የረዠም ጊዜ መጠራጠር ነገሮችን እንዲህ ቀላል አያደርጋቸዉም፡፡

ዋናዉ እና አሳሳቢዉ ፕራይቬታይዜሽን የሚለዉ ነዉ፡፡ በርግጥ የዘመኑ ኢኮኖሚ የሚመርጠዉ መንግስት ገቢያዉን ሪጉሌት እንዲያደርግ እንጅ እራሱ እንዲነግድ አይደለም፡፡ ለኢኮኖሚ እድገት፤ ፈጠራን ለማበረታታት፤ entrepreneurnial society ለመፍጠር ኢኮኖሚዉ በግሉ ሴክተር ቢያዝ የተሻለ ይሆናል፡፡ economic efficiency እንዲኖር ያደርጋል በመንግስት የእጁ መርዘም በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ያለዉን market failure ይቀንሳል፡፡ ከዶላር ማግኘት ምናምን በተጨማሪ ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛዉን ላገር ዉስጥ ባለሃብት ሲባል ምን ማለት ነዉ፡፡ ኤፈርት ስኳር ኮርፖሬሽንን ይገዛል፡፡ ከኤፈርት ዉስጥ ደግሞ ሱር የሚባለዉ የመንገድ ተቋራጭ ከአንድ ከዉጪ ኩባንያ ጋር ተሻርኩ ብሎ አየር መንገድን ይገዛል፡፡ አዜብ አስናቀ እና አዜብ መስፍን ስራቸዉን ለቀዉ አንድ ሁለት ፈረንጆች ጨምረዉ የሆነ ካምፓኒ ያቋቁሙና ግልግል ጊቤን የሃይል ማመንጫ ይገዛሉ፡፡ አባይ ጸሀየ ከክንፈ ዳኛዉ ጋር ይሆኑ እና እንደዚሁ የተወሰኑ ባለሙያወች ጨምረዉ የሆነ ካምፓኒ አቋቁመዉ ስኳር ኮርፖሬሽንን ወይንም ቴሌን ይገዛሉ፡፡ ልክ ከዚህ በፊት ፕሪቬታይዝ ተደረገ እየተባለ ሆቴሎች እና ፋብሪካዉች በሙሉ ለአላሙዲዉ ሚድሮክ እና ኤፈርት እንደተሸጠዉ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ስለዚህም በዚህ ወቅት ተጠቃሚዎች እንዳለ የህወሃት ካምፓኒ እና የህወሃት ባለሃብቶች ናቸዉ፡፡ ሌላ የአማራ ባለሃብት አየር መንገድ ሚገዛ ማነዉ፡፡ ወይስ የኦሮሞ ባለሃበት ምድር ባቡርን የሚገዛ ማነዉ፡፡ ስለዚህም ብአዴንና ኦህዴድ ምንድን ነዉ ተስማምተዉ የወጡት?? የኢኮኖሚ ባለሙያወችን አማክረዋል ወይ?? የአማራ እና ኦሮሞ ህዝብ እኮ ከነዚህ ዋና የኢኮኖሚ ምንጮች አልተጠቀምንም መጠቀም አለብን ብሎ ጥያቄ ሲያነሳ ነዉ ወደ ግል ይዘዋወሩ የሚባሉት፡፡ ለግል ተብለዉ ለህወሃት ባለሃብቶችና ካምፓኒወች የሚሰጥ ከሆነ ደግሞ ነገር ጭራሽ ተበላሸ፡፡ እኒህን ድርጅቶች እስካሁን ህወሃቶች ናቸዉ ያስተዳደሯቸዉ በመሆኑም inefficient ሁነዉ ቆይተዋል፡፡ አሁን ለነዚህ ሰወች ሲዘዋወር በምን መልኩ ነዉ የተሻለ ጥራት ያለዉ አገልግሎት የሚሰጡት??

መጀመሪያ እነ ጥረት እነ ኤፈርት መሸጥ አለባቸዉ፡፡ እነሱም ለሽያጭ መቅረብ አለባቸዉ፡፡

ለምሳሌ ባለፈዉ አመት ብአዴን ከመብራት አልተጠቀምኩም ሰብ ስቴሽን አልተሰራልኝም ብሎ ነበር፡፡ አሁን የመብራት ሃይል ዳይረክተሯ ጀርመን ባለት የ 150 ሚሊየን ዶላር ከተወሰኑ ሸሪኮቿ ጋር ሁና ጣና በለስን ገዛችዉ እንበል፡፡ እሷ ትርፍ ትፈልጋለች፡፡ ስለዚህ ወደ ሱዳን ወስዳ ነዉ መሸጥ የምትፈልገዉ፡፡ ያኔም ብአዴን ሊያለቃቅስ ነዉ ወይ ከመብራት ተጠቃሚ አይደለሁም ብሎ፡፡ ይሄን ነገር እንዴት እንደሚፈጸም መክሮበታል ወይ??

እኔ እንደመፍትሄ የሚመስለኝ አኒህ የኢንዶዉመንት ካምፓኒዎች መሳተፍ የለባቸዉም፡፡ መታገድ አለባቸዉ፡፡ ባለሃብቶች ከተወሰነ ፐርሰንት ሸር በላይ መያዝ የለባቸዉም፡፡ ለምሳሌ ከ 10 ወይም ከ15 በመቶ የማይበልጥ ሸር ብቻ እንዲኖራቸዉ ማድረግ፡፡ ተራዉ ዜጋ በበኩሉ ከነዚህ ድርጅቶች ሸር የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸት፡፡ ለምሳሌ ከ 25 እስከ 30 በመቶ ለተራዉ ህዝብ አክሲወን እንዲኖረዉ ማድረግ፡፡

ብቻ ይሄ ነገር እንቅልፍ ይነሳል፡፡ 27 አመት የተዘረፈ ገንዘብ አሁን ደግሞ በጓሮ በር የሃገሪቱን ዋና የኢኮኖሚ መስመር የሚባሉትን ህወሃት ሊወስደዉ ነዉ፡፡ ፕራይቬታይዜሽኑ የሚደገፍ ሆኖ አፈጻጸሙ ግን አደገኛ እና ለህዝብ የማይጠቅም አካሄድ ሊሆን ይችላል፡፡የተስማሙበትን አካሄድ ለህዝብ ማሳወቅ አለባቸዉ፡፡

(ሚኪ አማራ)

Share.

About Author

Leave A Reply