ቦንጋ፤ የቡና መገኛ ባለቤትነት ያስከተለው ውዝግብ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በደቡብ ክልሏ የቦንጋ እና በኦሮሚያዋ ጅማ ከተሞች መካከል የቡና መገኛ ባለቤትነት ዕውቅና ሰበብ መንገዶች ከትናንት ጀምሮ መዘጋታቸው ተሰማ። የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎችም በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። በቦንጋ እና በጅማ መካከል ውዝግቡ የጀመረው የቀድሞው ፕሬዝደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቦንጋ ከተማ ላይ ብሔራዊ የቡና ቤተ መዘክር ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ከጣሉበት ከ1999ዓ,ም ጀምሮ መሆኑን የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየው የላከልን ዘገባ ያስረዳል። በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በበኩላቸው በጅማ ዞን ተመሳሳይ ይዘት ያለው የቤተ መዘክር የመሠረት ድንጋይ ማኖራቸውንም ይጠቅሳል። የአሁኑን ውዝግብ የቀሰቀሰው የፌደራል ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዓመታዊ የቡና ፌስቲቫልን በተመለከተ ያደረገው እንቅስቃሴ መሆኑን የሸዋንግዛው አጭር ዘገባ ያመለክታል። DW ያነጋገራቸው በከፋ ዞን የባህል ቱሪዝም እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አቶ አስረስ ሃዳሮ የከተማዋ ነዋሪዎች ያሰሙት ቅሬታ ተገቢነት ያለው እና የዞኑ አስተዳደር አቋም ጭም መሆኑን ገልጸዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply