ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

Top of Form

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ነጂዎች ባነሱት የጥቅማጥቅም ጥያቄ ጋር በተያያዘ በትላንትናው እለት

ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገለፀ።

Bottom of Form

የኮርፖሬሽኑ ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ እንደገለፁት፥

የባቡር ነጂዎች ባነሷቸው የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ዙሪያ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ የ

አዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከሰራተኞቹ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በተነሱ ጥያቄዎች መግባባት ላይ መድረስ በመቻሉ ተቋርጦ የነበረው የባቡር ትራንስፖርት አገልገሎት

ከሐምሌ 11 ቀን 2010ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ጀምሮ በከፊልና ሐምሌ12 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ከጥዋቱ 12፡00 ጀምሮ

ከባቡር ነጂዎች ጋር በተደረሰ መግባባት ከሰሜን-ደቡብ ስምንት (8) ባቡሮች ከምስራቅ-ምዕራብ 11 ባቡሮች በድምሩ 19 ባቡሮች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት የትራንስፖርት አበል ብር 500 የሙያ አበል እንደየደረጃቸው ከ1 ሺህ ብር እስከ 1 ሺህ 500 እንዲከፈላቸው ማናጅመንቱ ወስኗል።

በተጨማሪም ለስራ ማነቃቂያ አበል ለደረጃ1 ባለሙያዎች ብር1 ሺህ 500፣ ደረጃ 2 ባለሙያዎች 700 በር ፣ ደረጃ 3 ባለሙያዎች 400 ብር እና የፈረቃ አበል የሚከፈላቸው ሲሆን፥

እንዲሁም ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰነውን የባቡር ነጂዎች እንዲያውቁ ተደርጓል ነው ያሉት።
ከዚህም በተጨማሪ ለካፍቴሪያ የምግብ ድጎማ 50%፣

የባቡር ትራንስፖርት በነፃ፣ የህክምና አመታዊ ወጪ 10 ሺብርና የ24 ሰዓት የህይወት ኢንሹራንስ ተግባራዊ እየተደረገ የነበረው በነበረበት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መድረስ መቻሉን አቶ ደረጀ ገልፀዋል።

ምንጭ፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን

 

Share.

About Author

Leave A Reply