ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ተመደበለት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቀድሞው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞትን ተከትሎ የግድቡን ግንባታ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን ላለፉት ሁለት ወራት በጊዚያዊነት በስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች ኃላፊነት የሰጡ ሲሆን፤ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳንና አቶ ፍቃዱ ከበደ ዳግም የግድቡ ምክትል ስራ አስፈጻሚዎች በመሆን እንዲያገለግሉ መመደባቸው ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply