ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መልዕክት አስተላለፈ “ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አጋርነታችንን በመግለጽ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል”

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በቅድሚያ የከበረ ሠላምታዬን እያቀረብኩኝ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያዊነትን በማፈንና ብሄራዊ ስሜትን በማደብዘዝ አገራችንን ለአደጋ ከዳረገው ስርአት ለመላቀቅና በምትኩ አንድነትን ፥ መተባበርን እና ፍትህን ለማስፈን ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ለማዳን በተለያየ አቅጣጫ ብዙ እንቅስቃሴዎች በሚካሄድበት በአሁኑ ወቅት፦

በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነትን እና ይቅር መባባልን ይዘው ብቅ ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና ባልደረቦቻቸው አጭር በሚባል የስልጣን ቆይታቸው ለወሰዶቸው በጎ እርምጃዎች እና ላሳዩን ኢትዮጵያዊ አለኝታነት አጋርነትን ማሳየት እና ከጎናቸው መቆም ጊዜው የሚጠይቀው አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ስገልፅ በሚደረጉት የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ላይ በሥራ አጋጣሚ በቦታው ባልገኝም በመንፈስ አብሬያችሁ መሆኔን ሳረጋግጥ በታላቅ ኢትዮጵያዊ ስሜት ነው።

ድል ለኢትዮጵያዊነት
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

 

Share.

About Author

Leave A Reply