ትናንት ማምሻውን ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የወንዞች ሙላት ምክንያት በስልጤ ዞን የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ትናንት ማምሻውን ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የወንዞች ሙላት ምክንያት #በስልጤ ዞን የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ 5615 ሰዎች በአደጋው ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን 637 ቤቶች ውስጥ ውሃ ገብቷል የተወሰኑ ቤቶችም ፈርሰዋል፡፡

የሞት አደጋው የደረሰው በቅበት ከተማ አስተዳደር የጠቀር ቀበሌና በስልጢ ወረዳ ሰነና ገሬራ ቀበሌ ሲሆን ከሟቾች ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ ከሚጓዙበት ባጃጅ ነው በወንዝ ውሃ የተወሰዱት፡፡

በአደጋው 1095 የቤት እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት ወድሟል 342 ሄክታር መሬት በውሃ ተይዟል፡፡ የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በስልጢ ወረዳና በቅበት ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ስድስት ቀበሌያት ነው፡፡

የዞን የወረዳና የቅበት ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተጎጂዎችን ጎብኝተዋል፡፡ የአደጋውን ተጎጂዎች የጎበኙት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ጥናት የሚያጠና የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ለተጎጂዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሄ ይሰጣል ብለዋል።

የስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ

Share.

About Author

Leave A Reply