ትናንት አልሸባብ በናይሮቢው ቅንጡ ሆቴል በፈጸመው የሽብር ጥቃት እስከአሁን 15 ሰዎች ተገድለዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በናይሮቢ ዱሲተ ዲ2 በተሰኘ ቅንጡ ሆቴል ላይ በተፈፀመ ጥቃት የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡ የምግብ ሬስቶራንቶችን፣ ቢሮዎችን እና ቅንጡ ሆቴልን በያዘው ህንፃ ላይ የታጠቁ ሀይሎች በትናንትናው ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነበር ጥቃት የከፈቱት፡፡

የመንግስት ባለስልጣናት ጥቃቱን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የገለጹ ቢሆንም እስከንጋት ድረስ የቶክስና ፍንዳታ ድምፅ በአካባቢው መሰማቱ ተገልጿል፡፡ አልሸባብ ጥቃቱ በተፈፀመ ደቂቃዎች ውስጥ ለሽብር ጥቃቱ ሃላፊነት መውሰዱን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ጥቃት 15 ሰዎች እንደተገደሉ የተገለጸ ቢሆንም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማረጋገጫ አልሰጡም ተብሏል፡፡ በጥቃቱ አንድ አሜሪካዊ መገደሉን የሀገሪቱ ውጭ ጉደይ መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ረጀም ሰዓታትን የፈጀውን ጥቃት የፈፀሙት ታጣቂዎች እጣ ፋንታም አልታወቀም ነው የተባለው፡፡ የሽብር ጥቃቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የተጀመረ ሲሆን ፥ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከመክፈታቸው በፊት በሆቴሉ መግቢያ በር ላይ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ቦምብ ማፈንዳታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የኬንያ ፓሊስ የሽብር ጥቃቱ የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት መሆኑን በትናትናው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

ጥቃት አድራሾች ሆቴሉ ሲገቡ የሚያሳይ የተንቃሳቀሽ ምስልም ተገኝቷል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም የፀጥታ አካላት በጥቃት የሚገኙ ሰዎችን የማዳን ስራ እየሰሩ እንደሚገኝ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Share.

About Author

Leave A Reply