ኖትረዳም እና ላሊበላ በዕድሜ እኩያ ናቸው:: ድህነት ክፉ ለተዘረጋልን እጅ ልንደርስለት አልቻልንም!

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከፈረንሳይ ታዋቂ የንግድ ስሞች ጀርባ ያሉት ቢሊየነሮች በከፊል የተቃጠለውን ኖትረዳም ካቴድራልን መልሶ ለመገንባት እስካሁን 300 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ገና ይቀጥላል። ገንዘቡ ብዙ ይመስላል (ለኛ)

ከአመት በፊት ላሊበላን ከመፍረስ ለማዳን የተጠየቀውን 300 ሚሊዮን ብር ለማዋጣት ግን አንድም የሃገሬ ሃብታም እጁን ኪሱ ስለመክተቱ አልሰማሁም። ቅርስ ጥበቃ እና ክልሉ በድምሩ 50 ሚሊዮን ብር ከማዋጣታቸው በቀር ከሃገር ውስጥ የተገኘ ድጋፍ ስለመኖሩ አልሰማሁም። ።

ያም ሆኖ ፈረንሳይ በደምሳሳው እኔ እጠግነዋለሁ ነው ያለችው።እስካሁን ግን ከቃል ያለፈ ተግባራዊ ምላሽ አልታየም።

ሃብታሙ ኖትረዳም ቀድሞ በነበረ መልኩ ተመልሶ ይገነባል እየተባለ ነው። ደሃው ላሊበላ ደግሞ እያየነው ከቀን ወደቀን የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት ቁጭ ብሏል።

ኖትረዳም እና ላሊበላ በዕድሜ እኩያ ናቸው። የካቶሊክ እና ኦርቶዶክስ ይሁኑ እንጂ ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። ላሊበላ ኖትረዳምን የሚልቅበት ታላቅ ነገር ከአነድ ወጥ ድንጋይ ብቻ ተፈለፍሎ መሰራቱ ነው። ይህ ትንግርት ነው። ኖትረዳም ደግሞ በድንቅ የስነህንጻ ጥበብ በብዙ ሲሚንቶ እና በብዙ ድንጋይ ተገንብቷል።

ላሊበላ ቢፈርስ ከዓለም የስነህንጻ አውቀት በላይ በመሆኑ በምንም መንገድ ተመልሶ አይገነባም።ኖትረዳም ግን ገንዘባቸውን ይጭነቀው እንጂ ተመልሶ ሊገነባ ይችላል። ሁለቱም በዩኔስኮ የተመዘገቡ የዓለም ቅርሶች ናቸው። ግን ደሃና ሃብታም ስለሆኑ ሃብታሙ ከበቂው በላይ የሆነ ድጋፍ እየጎረፈለት ነው። ደሃው ግን የእግዚአብሄርን ቸርነት እየጠበቀ ይኸው እለ።

መላኩ ብርሀኑ

Share.

About Author

Leave A Reply