አርበኞች ግንቦት 7 ማንኛውንም ዓይነት ሰላማዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ ማቆሙን ይፋ አደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ማንኛውንም ዓይነት ሰላማዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ ማቆሙን ይፋ አደረገ።

ንቅናቄው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በማናቸውም መልኩ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ምንም ዓይነት አመፅ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መታቀቡን አስታውቋል።

በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ አባላቱም ከማናቸውም የአመፅ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡም ንቅናቄው ድርጅታዊ ትእዛዝ አስተላልፏል።

ንቅናቄው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ መሪነት በሀገሪቱ ውስጥ እየተወሰደ ባለው እጅግ አበረታች እንቅስቃሴ የሀገሪቱን ፖለቲካ ከአመፅ ነፃ በሆነ ሰላማዊና ስልጡን ፖለቲካ ከግብ ማድረስ እንደሚቻል ተስፋ ስለፈነጠቀ ውሳኔውን ማሳለፉን አስታውቋል።

የንቅናቄው ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን አበረታች እንቅስቃሴ ለማገዝ በልዩ ስብሰባው ይህንን ውሳኔ እንዳሳለፈም ነው የገለፀው።

አርበኞች ግንቦት 7 በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ቡድንነት የተመዘገበ ድርጅት ቢሆንም፥ በቅርቡ ለምክር ቤቱ የቀረበውና በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የምህረት አሰጣጥና አፈፃፀም ረቂቅ አዋጅ ድርጅቱ ምህረት እንዲደረግለት የሚያስችል ነው።

 

Share.

About Author

Leave A Reply