አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በአዲስ አበባ ዙሪያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለተፈናቀሉ ዜገጎች በዛሬው ዕለት የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ፡፡

በወቅቱ በመድሃኒዓለም ት/ቤት አስተዳደሩን ወክለው የተገኙት የማህበራዊ ክላስተር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ከድር አርቲስቱ በቼክ ያበረከተውን ድጋፍ በዓይነት ተቀይሮ ለተጎጂዎች የቁሳቁስ ድጋፍ መልክ እንዲሰጥ በወሰነው መሰረት ለአርቲስቶች አስተባበሪ አቶ ያሬድ ሹመቴ አስረክበዋል፡፡

በዚህም ለተጎዱ ወገኖች የምግብና አስፈላጊው የቁሳቁስ ድጋፍ በአፋጣኝ እንደሚደርሳቸው እንደሚያደርግ ተመልክቷል፡፡

አርቲስት ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የተጎዱ ወገኖቻችን ከችግር ለመታደግ ላሳየው ቅን ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስጋና ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply