አቡነ መርቆርዮስን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ ይቅርታ አደረጉ፡፡ አቶ ታምራትም ሃሳባቸውን በገፃቸው እንደሚከተለው አስፍረዋል፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“እስር ቤት ሳለሁ ከተመኘኋቸውና ስጸልይም ከነበርኩባቸው

ጉዳዮች አንዱን በዛሬው እለት እግዚአብሄር ፈቃዱ ሆኖ

አከናወነልኝ። ከስር በፎቶው እንደሚታየው ብጹእ ወቅዱስ አቡነ

መርቆሬዎስን ባረፉበት ቦታ፣ አራት ኪሎ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሄጄ

አገኘኋቸው።

ጎንበስ በማለት ጉልበታቸውን ስሜ፣ በጌታችንና በመድሀኒታችን

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይቅር እንዲሉኝ ጠየቅኋቸው። (ሳይወዱ

በግድ፣ ብዙ ማስፈራሪያና እንግልት ደርሶባቸው፣ ከአገር

የወጡት በአቶ መለስ ትእዛዝ፣ በአቶ ክንፈ አቀናባሪነትና

ማስፈራራት፣ በእኔ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ነበር)።

እርሳቸውም በደስታ ተቀብለው፣ በይቅርታ መረቁኝ።

እግዚአብሄርን እያመሰገኑ ባረኩኝ። በፍቅር መንፈስ ሆነን

በተቃቀፍን ጊዜ በእውነት በእግዚአብሄር ቸርነትና በርህራሄው

ስንደመም ተሰማኝ። ከልቤ እጅጉን አመሰገኋቸው፣ አክብሮቴንም

ገለጽኩላቸው። ከጠበቅኩት ባለፈ የአባትነት ፍቅራቸውን

ከልባቸው በይቅርታ ስለቸሩኝ ይበልጡን ልቤ ታድሷል፤ ” ይላሉ ፈርመው ያባረሯቸው አቶ ታምራት ላይኔ፡፡

አቡነ መርቆርዮስ መስከረም 30 ቀን 1984 ዓም የህወሓት ደህንነት ከፕትርክናቸው አስነስቶ አባታዊ ክብራቸውን በማይመጥን ሁኔታ አባሯቸዋል፡፡ለዚህ ሁሉ አስፈፃሚው እኔ ነኝ የሚሉት የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበር፣የመከላከያ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ዛሬ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

አቡነ መርቆርዮስ መስከረም 30 ቀን 1985 ዓም ከአዲስ አበባ አስራ አንድ ሰዓት ጠዋት ተነስተው ጥቅምት አንድ 1985 ምያሌ ደርሰዋል፡፡ ሞያሌ ደርሰው የኬኒያ በሬ ነጋዴዎች እሳቸውን ጋቢና ላይ፣ሌሎች ጳጳሳትን ከከብቶች ጋር በውጭ በጭነት መኪና አሳፍረው ናይሮቢ አድርሰዋቸዋል፡፡ ከምያሌ ናይሮቢ ከ 500 ኪሜ በላይ ይርቃል፡፡ይሄን ሁሉ መንገድ በጭነት መኪና ተጉዘው ናይሮቢ ደርሰዋል፡፡

አቡነ መርቆርዮስን ከአዲስ አበባ ያሸሻቸው ሹፊር አብሯቸው እስከ ኬኒያ ሂዶ በኬኒያ በወባ ሙቶ ሳይመለስ ቀርቷል፡፡ስሙ መሃሪ ይባቤ ይባላል፡፡

ከ 5 ዓመት ኬኒያ ቆይታ በኃላ ብፁኡነታቸው ወደ አሜሪካ ሲያትል አቀኑ፡፡በአሜሪካም የሃይማኖት አባቶችን ሰብሰበው ሲኖዶስ አቋቋሙ፡፡

ደርግ ናቸው ተብለው በህወሓት መከራ የከፈሉት አቡነ መርቆርዮስ በጠሚዶ አብይ አህመድ አማካኝነት አብነት የተማሩባትን ምድር ከ 16 ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ረግጠዋል፡፡

ህዋኃት የክፉነት ታሪኩን በቁሙ ያፃፈ ብቸኛ ድርጅት ሆኗል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply