አትሌት ሙሉ ሰቦቃ በዳሊያን ማራቶን አሸነፈች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አትሌት ሙሉ ሰቦቃ በቻይና በተካሄደው የዳሊያን ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር አሸነፈች።

አትሌት ሙሉ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃለች።

በውድድሩ ኬንያውያኑ አትሌቶች ኤድናህ ሙክዋናህ እና ሮዳህ ጄፕኮሪር ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በወንዶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ ኬንያዊው ኤድዊን ኪቤት ኮኤች 2 ሰዓት ከዘጠኝ ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

አትሌቱ በሃገሩ ልጅ ጁሊየስ ማይሴይ የተያዘውን የቦታውን ክብረ ወሰንም በ44 ሰከንድ አሻሽሎታል።

ኬንያዊው ዊሊ ንግሌል እና ኢትዮጵያዊው ሀብታሙ ወጊ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

በውድድሩ ለአሸናፊዎች 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ምንጭ፦ ሺንዋ

 

Share.

About Author

Leave A Reply