አቶ ለማ መገርሳ 1500 የአመራር አባላትን ከስልጣን አባረው 500 አባላት ከደረጃቸው ዝቅ አደረጉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ስምንተኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበርና የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኮንፈረንሱ ማጠቃላይ ላይ ለመገኘት አዳማ ገብተዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ካለፈው እሁድ አንስቶ ስምንተኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንሱን በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ ድርጅቱ የተለያዩ ፈተናዎችን እያለፈ ውጤት ማስመዝገብ ጀምሯል ሲሉ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡

ኦህዴድ የህዝቡን ጥቅም ይበልጥ ለማስከበር መዘጋጀት አለበትም ብለዋል፡፡

የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ደግሞ በድርጅቱ አመራር እና አባላት ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማረም ግምገማ መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡

ይህንኑ ግምገማ ተከትሎ በተለያየ ደረጃ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 500 የአመራር አባላት ከስልጣን መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡

540 ሃላፊዎች ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች በአዲስ አመራርነት እንዲሾሙ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ ሁለት ሺህ የድርጅቱ አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply