አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሣ መብትን መጨፍለቂያ “መብት” ማን ሠጣቸው? (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“የአዲስ አበባ ህዝብ የራስን እድል የመወሰን መብት የለዉም”

(አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሣ-የኦህዴድ ቃል አቀባይ)

“የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት”

አንቀጽ 49

ርዕሰ ከተማ

  1. የፌደራሉ መንግስት ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ነው::

2.የአዲስ አበባ አስተዳደር ራሱን በራሱየማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል::

  1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥት ይሆናል::

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዚህ ህገ መንግስት በተደነገገው መሰረት በፌደራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይወከላሉ::” ይላል::

አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንቀጽ 49 ን.አ. 2 “ራሱን በራሱየማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን” በነሱ

“ሕገ መንግስት”የአዲስ አበባ ህዝብ “የተፈቀደለትን” ዕድልና መብት እሳቸው እንደሚወስኑ እየነገሩን ነው:: የራሣቸውን “ሕገ መንግስት” “በቻርተሩ” መተካቱ ይሆን?

ትብስን ልንተካ እንዳይሆን እፈራለሁ?

አዲሱ አረጋ በነዚህ ምክንያቶች ልክ ናቸው::

ሀ). አቶ አዲሱ አረጋ! በትክክል የአዲስ አበባ ህዝብ የራስን እድል የመወሰን መብት የለውም:: መብቱ በአምባገነናዊው ሥርዐት በጉልበት ስለተገፈፈ::

ለ). የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህ መብት ቢኖረው ኖሮ አምባገነኖች ያፈኑትን መብትና ነፃነትን “ነገም አታገኝም” ብለው አዲሱ አረጋ ቂጤሣ በአምባገነንነት ባልተናገሩ ነበር::

ሐ). የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህ መብት ቢኖረው ኖሮ ያልመረጣቸውና የማይወክሉት ሹሞች ባልመሩት ነበር::

መ). የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህ መብት ቢኖረው ኖሮ ያልመረጣቸውና የማይወክሉት ግለሰቦች አምባገነናዊ እብሪታቸውን በነፃነቱና በመብቱ ላይ ሊጭኑ ባልቃጣቸው ነበር::

ሠ). የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህ መብት ቢኖረው ኖሮ መብቱን የሚነፍጉትን አምባገነን ባለሟሎች ድንፋታን ባላየና ባልሰማ ነበር::

ረ). የአዲስ አበባ ህዝብ ለዚህም ነው እንደሌላው ኢትዮጵያዊ መብትና ነፃነቱን የሚያጎናፅፈውን የዴሞክራሲ ስርዐት ለማንገሥ የሚዋደቀው::

“የአዲስ አበባ ህዝብ የራስን እድል የመወሰን መብት የለውም” የሚሉን አምባገነኖችና አምላኪዎቹን የተንገዳገደውን የአፓርታይዳዊ አገዛዝ ጠግነውና ሌላ አምባገነን ሆነው የአዲስ አበባ ህዝብን ዕድል እነሱ መወሠንና አዲስ አምባገነን መሆን ካማራቸው የአዲስ አበባ ህዝብ በነፃነቱ ትግል የነርሱን “ያልወከላቸውን ሕዝብ ዕድል “የመወሰን” እብሪታቸውን ያመክነዋል::

ለዚህ ነው እራሣቸውን ነፃ ያላወጡና በአምባገነኖች ተኮትኩተው ያደጉ ግልገል አምባገነኖች እንዴት ሃገርን ይቀይራሉ የምንለው። እንዴትስ ነው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዐት እጅ ይሰጣሉ ብለን የምንደፍረው? እያለ ሕዝቡ የሚጠይቀው::

አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሣ ምናልባትም የጥቂቶችን ጎሣዊ አፓርታይዳዊ ስርዐትን ‘በብዙሃን አምባገነንነት’ ለመተካት ሲያልሙ አድረው ከሆነ ጊዜው የዴሞክራሲ ነውና እንደገና እንዳያቃዣቸው እንቅልፍዎን ይጨርሱ እንላለን::

We don’t need neither a numerical minority ‘Apartheid system nor a numerical ‘tyranny of dictatorship’.

What we need is DEMOCRACY. PERIOD!

Share.

About Author

Leave A Reply