አንድ የአገር ውስጥ ኩባንያ ለወንጂ ስኳር 11 ቢሊዮን አቀረበ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አንድ የአገር ውስጥ ኩባንያ ወንጂ ስኳር ፋብሪካን ለመግዛት 11 ቢሊዮን ብር ለመንግስት አቀረበ፡፡ ፎርቹን ጋዜጣ በትናንት እትሙ እንደዘገበው ኢትዮ ሹገር ማኑፋክቸሪንግ ሼር ኩባንያ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤትና ለስኳር ኮርፖሬሽን በፃፈው ደብዳቤ ፋብሪካውን መግዛት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

ጥያቄው በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ስር ያሉትን ሁለት ፋብሪካዎችና በ12 800 ሄክታር ላይ ያረፈውን የሸንኮራ አገዳ ሰብል የሚካትት ነው፡፡ ፋብሪካው በአሁኑ ሰአት በአመት 174 ሺህ ቶ ስኳር የማምረት አቅም ያለው ነው፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ሃላፊው አቶ ጋሻው አይችሉህም በተጠቀሰው ዋጋ የተጠቀሰው ኩባንያ ፋብሪካውን ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቡን ለፎርቹን አረጋግጠዋል፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ ከገዢው ጋር ድርድር ለማድረግ የሚያስችለው ሶስት አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዳዋቀረ አስረድተዋል፡፡ ኮሚቴው ሽያጩን ገምግሞ የይሁንታ ምክረሃሳብ ካቀረበ ማኔጅመንቱ ይመለከተውና ለመጨረሻ ውሳኔ ለቦርዱ እንደሚያስተላልፈው ከጋዜጣው ዘገባ ለመረዳት ችለናል፡፡ ኢትዮ ሹገር ማኑፋክቸሪንግ ሼር ኩባንያ ከተቋቋመ ሶስት ወር ያስቆጠረ ኩባንያ ሲሆን የተመሰረተው በ24 ባለአክሲዮኖች ነው፡፡

የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሽያጭ ከመንግስት ይሁንታን ካገኘ 11 ቢሊዮን ብሩን አክሲዮን በመሸጥና ከባንክ በሚገኝ ብድር እንዲሁም ኤችቪ ኤ የተሰኘውን የሆላንድ ኩባንያ በማስገባት አሟልቶ እንደሚከፍል ተናግሯል፡፡ ከዚህ ቀደም ወንጂ ስኳር ፋብሪካን ህብር ስኳር የተባለና ሳይቋቋም የፈረሰው ድርጅት ለመግዛት ሞክሮ ሳይሳካለት መቅረቱ ይታወሳል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply