አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ስፍራ ስያሜው “ቱሉ ፈራ” ወይም “መጥፎ ዕድል” ተብሎ እንደሚጠራ ያውቃሉ?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን “ቱሉ ፈራ” በተባለ አካባቢ (ጊምቢቹ ወረዳ) ተከሰከሰ፡፡ በአደጋው አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 157 ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው አጡ ፤ ዜናውም መላውን አለም አሳዘነ፡፡

የአውሮፕላኑ አደጋ እና አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ቦታ ስያሜ (ቱሉ ፈራ) ግጥምጥሞሽ መፍጠራቸው ደግሞ ብዙዎችን እያስገረመ ነው፡፡ ‘ቱሉ ፈራ’ የሚለው የኦሮምኛ ቃል ‘መጥፎ ዕድል’ እንደማለት ነው፡፡

ስፍራው ይህን ስያሜ እንዴት ሊያገኝ እንደቻለ ቢቢሲ አማርኛ የአካባቢውን አዛውንቶች ጠይቆ ነበር፡፡ አቶ ባትሪ ለማ የተባሉ የአካባቢው አዛውንት “ቱሉ ፈራ ይህን ስም ያገኘው በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ነው” ይላሉ።

“ቦታው ከፍታማ ስለሆነ የንፋሱ አቅጣጫ ወዴት እንደሚነፍስ ለማወቅ ያስቸግራል” የሚሉት አቶ ባትሪ “በስፍራው ያለው ቅዝቃዜ ኃይለኛ በመሆኑ ሰዎች ተራራው ላይ መኖር ሲያቅታቸው ቱሉ ፈራ ብለው ሰየሙት። ትርጉሙም በአማርኛ የመጥፎ እድል ማለት ነው” ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ባትሪ አገላለፅ የአካባቢው ቦታዎች በሙሉ የተሰየሙት ባለው የአየር ሁኔታ ላይ ተመስርተው ነው። ለምሳሌ አውሮፕላን የወደቀበት ቦታ ሃማ ይባላል። ይህ ማለት ክፉ ወይም መጥፎ ማለት ነው።

በአካባቢው የሚገኝ ተራራ ደግሞ ፈራ ተራራ ይባላል። አውሮፕላኑ ከወደቀበት ቦታ ቀጥሎ ያለው ደግሞ ነኑ እኩቢ ሲባል የበሽታ አካባቢ ማለት እንደሆነ አቶ ባትሪ ያስረዳሉ።

በኦሮሚኛ ቱሉ ፈራ የሚሉት ቃላት በቀጥታ ሲተረጎሙ “መጥፎ ዕድል” የሚል ትርጉምን ይይዛሉ። በእርግጥም በአካባቢው ያጋጠመው አደጋ ሰለባዎች መጥፎ እድል ገጥሟቸው ሃዘኑ ከሃገር አልፎ ለዓለም ተርፏል።

ምንጭ – ቢቢሲ አማርኛ

Share.

About Author

Leave A Reply