አየር መንገዱ እውን የኢትዮጵያ ነው?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከሁለት አመት በፊት ነው! የትህነግ/ህወሓት ባለሀብቶች ብረት በርካሽ ዋጋ ይፈልጋሉ። ሊሸጡት ነውኮ! ሲያስቡ በህሊናቸው ከትህነግ ጎን በመሆናቸው ብቻ እንደቤታቸው የሚያዩት አየር መንገድ ይመጣላቸዋል። ወደ አየር መንገዱ ኃላፊ ተወልደ ዘንድ ይሄዳሉ። የጋራዡን ጉዳይ የሚቆጣጠረው ሰው እንዲጠይቁት ይልካቸዋል።

የጋራዥ ኃላፊውን ሲጠይቁት ፈቃደኛ አልሆነም። ብረቶቹ የሚመጡት ከቀረጥ ነፃ ነው። ከአየር መንገዱ ብቻ ነው። የትህነግ ባለሀብቶች ደግሞ ይህን በነፃ የመጣ ብረት በውድ መሸጥ ይፈልጋሉ።

በእርግጥ በግላቸው አይደለም የጠየቁት። የብረታብረት ኮርፖሬሽን እንደሚፈልገው አድርገው ሰነድ አቅርበዋል። የጋራዡ ኃላፊ አልፈቅድላቸው ሲል ወደ ተወልደ አቀኑ። ተወልደ ለጋራዥ ኃላፊው ደብዳቤ ፃፈ! ይሰጣቸው ብሎ! የጋራዥ ኃላፊው ደብዳቤውን ይዞ ብረቱን እንዲወስዱ አደረገ። ምን አማራጭ አለው?

ከጊዜ በኋላ ጉምሩክ ከአየር መንገድ ውጭ ማንም የማያስገባቸው ብረቶችን መርካቶ ያገኛል። የአየር መንገድ ጋራዥ ኃላፊው ይታሰራል። እሱ የተወልደን ደብዳቤ ይዟል። ስለዚህ ነፃ ተባለ። ወደ እነ ተወልደ መዝለቅ አይቻልም።

~ኃይለመድህን አበራ አውሮፕላን ይዞ የጠፋው ሀገሩን ስለሚጠላ አይደለም። አየር መንገዱ የአንድ ቡድን ስለሆነ ነው! የትህነግ! የቡድን፣ የትህነግ!

~አንድ ቴክኒሻን ለምን ከነዳጅ በርሜል ስር ተደብቆ ጠፋ? አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ስላልሆነ ነው! በዓዳ ከሆነ ቆይቷል!

~ለመሆኑ አንድ የአየር መንገድ ቴክኒሻን፣ ፓይለት፣ ሌሎችም ሰራተኞች የሚከፈላቸው አየር መንገዱ ከሚያገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር ብዝበዛው በባርነት የመኖር ያህል አይደለም?

(ጌታቸው ሽፈራው)

Share.

About Author

Leave A Reply