አዲሱ የኢትዮጵያ ባርነት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በቅርቡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ሬክስ ቲለርሰን ወደ አፍሪካ አገራት ኬኒያ፣ ቻድና ቻይና ጉብኝት አድርገው ነበር በቆይታቸውም የታዘቡትን የቻይኛ አፍሪካ አገራትን በተፈጥሮ ሃብት ለመቆጣጠር በምታደርገው ድጋፍና ብድር የመንግስታቱን ራስ ገዝነት በማዳከም ወደአዲስ የቅኝ ግዛትነት በመቀየር ላይ መሆኑዋን አበክረው ተናግረው ነበር፡፡በጊዜው የአሜሪካን የበላይነት አቅም ለመገልበጥ በኢኮኖሚ ተቀነቀቃኝነት ለምትሰየመዋ ቻይና የጥላቻ መልእክት እንደሆነ ተተርጉሞ ተወሰደ በርግጥም ግን መልእክቱን በኢትዮጵያዊነት ላስተዋለው ብዙ የእውነታ ማሳያ ተጨባጭ መረጃዎች ነበሩት

ለምሳሌ

  • አዲሱ የአፍሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ በቻይና እርዳታ ተሰርቶ በአመቱ ማፍሰስ ጀመሮ ነበር የባስው ደግሞ በአዳራሹ በየመቀመጫዎቹ ስር የተደበቁ መቅረፀ ድምፆች መገኘታቸው ሲሆን ይህን መረጃ በሚዲያ ተነግሮም እንደቀላል ተወስዶ ነበር
  • በሚሰጡት ብድርና እርዳታ ብዙ ግዜ ተጠቃሚ እንደሆኑ ቢታወቅም እስከታች የጉልበት ሰራተኞችን በቻይናውያን የማሰራት እንዲሁም በጣም ፍትሃዊነት የጎደለው ክፍያና በየፋብሪካቸው የሚታየው የኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የመብት ጥሰት ሀይ ባይ ያጣ ችግር ነው
  • በተለይም አንድ ሁለት ተብሎ ያልተነገረለት የኢትዮጵያ ማእድናትና ጥሬ ሀብት ፍለጋና ግኝቱ በሚስጥራዊነት መያዙ ካገኘነው ይልቅ ያጣነውን ያገዝፈዋል በዛ ላይ በፍለጋውም ሆነ ዙሪያ ገባው በየዘርፉ ከትንሽ እስከ ተላልቅ ፕሮጀክቶችን በቻይናውያን ተይዞ ባለበት ሁኔታ!
  • የወጭ ንግድን እንኳን ስንመለከት የቅባት እህሎችን በተለይም ሰሊጥ ከ85% ወደቻይና የሚላክ በጥቂት የቻይና ካምፓኒዎች በበላነይነትና በዋነኝነት በመያዙ ምክንያት በዝቅተኛ ዋጋ ለመላክ ከመገደዳቸውም በላይ የላኪዎች የዋጋ መደራደሪያ አቅም በጥያቄ ውስጥ ነው
  • መርካቶ ውስጥ ከአከፋፋይነት እስከ ችርቻሮ በራሳቸው ዜጎች የንግድ መረብ አይረቤ እቃዎችን በርካሽ ዋጋ በማሰራጨት በጥሩ ደረጃ የተመረቱትን አስመስሎ በመስራት ከጥቂት ራስ ወዳድ መጤ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ሁነኛና ነባር ነጋዴዎችን ከገበያ በማስወጣት ስራ ተዐምደው ይገኛሉ
  • በተጨማሪም የቻይና ሰራሽ የባቡር እንዲሁም በየድርጅቱ እየገቡ ያሉ ከባድና ቀላል ማምረቻ ማሽኖች መቀየሪያ እንዳይኖራቸውና በሌሎች አገራት ባለሙያዎች መጠገን በማይችሉበት መንገድ ሰርተው በማስገባት የቻይናው አምራች ድርጅት ብቻ ሊጠግንና ቅያሪ መሳሪያዎችም ከፋብሪካው ብቻ እንዲገዛ በሚየመቻች ሁኔታ ዋጋ ቀነስ አድረጎ በጠቅላይነት መያዝ ብሎም ከስራው ባለቤቶች ጋር ለማዋሀድ ሲባል ለረጅም ግዜ ከፍተኛ ተከፋይ ሰራተኞቻቸውን ከቻይና በማስመጣት በተቻላቸው አቅም ግዛታቸው ውሰጥ በማስገባት ላይ ናቸው፡፡
  • (AGOA)አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት ከቀረጥ ነፃ የግብት እድል ሰጥታለች በቅርቡ አሜሪካ ከቻይና የምታስገባው ግብይት ደግሞ ከፍተኛ ቀረጥ ተጥሎበታል በመሆኑም የኢትዮጵያን እድል በኢንደስትሪ መንደሩ በኩል በእጅ አዙር ቻይንዮ ትጠቀምበታለች በቅድሚያ የኢትዮጵያን ጥቅምን ሚያስከብር መንግስት ፖሊሲና አስተዋይ ትውልድ ያስፈልገናል ባይ ነኝ፡፡

(እየሩስ ሀድጉ)

Share.

About Author

Leave A Reply