Thursday, January 17

አፓርታይድ በወልቃይት ምድር

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(ቢትወድድ መ. ብርሀኔ)

በ2008 ዓ/ም ዳንሻ የ11ኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ግዜ አንድ መምህር በርሀ የሚባል የሒሳብ አስተማሪያችን ነበር፡፡እናም ይሄ አስተማሪያችን በሒሳብ ጥሩ ውጤት እንዲኖረን ከመደበኛ ክላስ ውጭ ሁሌም ሀሙስ ሀሙስ ያስተምረን ነበር፡፡ ግዜው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ባገኘው አጋጣሚ አማራነቱን የሚያሳይበት ግዜ ስለነበር ለምን አማራ ነኝ ብለህ ለስብሰባ ጎንደር ሄድክ በሚል ሰበብ ሊላይ ብርሃኔን ባፈኑት ግዜ የዳንሻ ከተማ ህዝብ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ሴቱ ወንዱ፣ሽማግሌው መነኩሴው ሳይቀር ወጥቶ ተቃውሞውን በአደባባይ መግለጹንና አማራነቱን በይፋ ማሳየቱን ማንም የሚዘነጋው አይደለም፡፡ በዚህ ሰልፍ ምክንያትም ከ9 ያላነሱ አማሮች ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ተሰቃይተውበታል፡፡ እና ያኔ ተማሪው ከትምህርት ቤት ቀርቶ ተቃውሞውን ተቀላቅሎ ነበር የዋለው:: በነገታው ክላስ ስንሄድ መምህሩ መጥቶ ከዚህ በኃላ ሀሙስ የምንማረውን ትምህርት እናቆመዋለን፣ አላስተምራችሁም ብሎ አሰናበተን በሱ ቤት አማራ ነን በማለታችን እየጎዳን መሆኑ ነው፡፡የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ሳይቀር ሰልፍ ላይ በጥቁር መኪና ነው ማሳፍናችሁ ብሎ የዛተውንና አማራ በመሆናችን የተሰደብነውማ ብዙ ነበር፡፡ በጣም በብዙ ነገርም ሊያሸማቅቁን ሞክረው ነበር፣ የታሪክ መምህሬና የክላስ ስም ጠሪዬ የነበረችው መምህር ሙሉ “ብትግራዋይነትካ አይትኮርዕን? ትግራዋይ እኮ እዩ ዓለም ዘሽክርክራ ዘሎ፡፡ እዚ ዘለካዮ መሬት እኮ ናይ ትግራይ እዩ፡፡”እና ሌላም እያለች በእናባርርሃለን ዓይነት ሙድ በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ያስፈረመችኝንማ አልረሳውም ፡፡ ሌሎችም ከሰልፉ ለምን ተሳተፋችሁ ተብለው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውና የተባረሩ ተማሪዎችም አሉ፡፡ ብቻ ብዙ ነገር አለ ላሁን ይብቃኝና አሁን መናገር ወደ ፈለግኩትን ሃሳብ ላምራ….

ይሄ ሁሉ ማለት የፈለግኩት ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ያን ግዜ የተጀመረው በቀል እየሰፋ ሂዶ ትልቅ ዋጋ እያስከፈለን ስላለ ነው፡፡ በዘንድሮው ዓመት ማለትም 2009 ዓ/ም ዳንሻ ላይ የተማሩ አብሮ አደግ ጓደኞቼ በትግራይ መምህራን ምን ያህል እየተሳቀቁ እንደተማሩ፣ያልገባቸውን እንኳን ሲጠይቁ እኔ የአንተ ቅጠረኛ መምህር አይደለሁም አንብበህ ተረዳ እየተባሉ፣በአማራነታቸው እየተሰደቡ፣ እንዲሁም አስፈላጊውን ትምህርት ሳያገኙ በመቅረታቸው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በጣም ዝቅተኛ ማምጣታቸው (ማለፊያው ባይታወቅም አብዛኛው ተማሪ ከ300 በታች በማምጣታቸው የሚያልፉት ጥቂቶች እንደሆኑ አያጠራጥርም፡፡) ውስጤ ስለደማ እንዲሁም ወያኔ ትውልድን በመግደል፣ትልቅ ደረጃ ላይ ይደርሳሉ የተባሉ ተማሪዎችን ተስፋ ባጭሩ በመቅጨት ወደ አጓጉል ህይወት እንዲገቡ በማድረግ ምን ያኽል እየተበቀለን እንዳለ ለማሳወቅ ነው፡፡

.የተፈታኞቹ ውጤት እንደሚከተለው ቀርቧል:-
~ጠቅላላ ተፈታኞች=126
~ከ400 በላይ=2
~ከ300 በላይ=46
~የተቀረው ማለት ከ300 በታች ደግሞ 78 ተማሪዎች
ማለት ነው::
.በመጨረሻም በዚህ ጉዳይ ላይ አማራ የሆነ ሁሉ ዝም ሊል አይገባም ባይ ነኝ::

 

Share.

About Author

Leave A Reply