“ኡቡንቱ” – አንዱ እያዘነ እንዴት ሌላው ደስተኛ ይሆናል? (አሰግድ ዮሀንስ ከደቡብ አፍሪካ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ወዴት እየሄድን እንደሆነ ባላቅም የመጣንበትን እንደረሳን ግን ቅንጣት ያክል ጥርጥር የለኝም። አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ውድ ህይወታቸውን ሰውተው ያቆዮልን ሃገር ላይ እንዴት በሰላም መኖር ከበደን?

ሁሉም ነገር የሚመነዘረው በብሔር፣ በዘር፣ በጎጥ ሆኗል። መጥበብ አዲሱ ፋሽናችን ነው። ሰው መግደል ቀልድ ሆኗል፣ አንገብጋቢው ነገር የገዳዮ ድርጊት ሳይሆን የገዳዮ ብሔር ሆኗል፣ መርዶ ስንሰማ ሀዘን ከመቀመጣችን በፊት የኛ ብሔር ተወላጅ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። አረ ወዴት እየሄድን ነው?

ባደጉ ሃገራት በዲግሪ የተመረቀውም፣ ፊደል ያልቆጠረውም አስተሳሰባቸው ቅንጣት ያህል አለመራራቁ እጅግ ያስደነግጣል። ሃገሬ ድረስና ልክ አሳይሃለሁ ማለት ፋሽን ከሆነ ሰነበተ። እኔ እንጂ እኛ ብሎ የሚናገር ሰው መስማት ብርቅ ሆኖብናል።

ሳውዝ አፍሪካኖች UBNTU የምትባል ደስ የምትል ታሪክ አላቸው። አንድ አንትሮፖሎጂስት ዛፍ ስር ሶስት ቅርጫት ከረሜላዎች ካስቀመጠ በኃላ ህፃናቱን መቶ ሜትር አርቋቸው። ለህፃናቱ ቀድሞ የደረሰ ሁሉንም ይውሰድ አላቸው። ህፃናቱ ግን እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድ ላይ በመሄድ ከረሜላዎቹን ዕኩል ተካፈሏቸው።

አንትሮፖሎጂስቱም ይሄን ለምን አረጋችሁ ብሎ ጠየቃቸው? ህፃናቱም ubuntu ብለው መለሱለት። ያ ማለትም ” እንዴት አንዱ ደስተኛ ይሆናል ሌላው እያዘነ” ማለት ነው፡Ubuntu በዙለኛ ትርጉሙ ” I am because we are” የሚል ጠንካራ ትርጉም አለው።

ታዲያ እኛም ለሃገራችን ኡቡንቱ እንበልላት።

Share.

About Author

Leave A Reply