Thursday, January 17

ኡጋንዳ ለአፍሪካ ነጻነት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሀገራት የምትሰጠውን ከፍተኛ ሜዳሊያ ነገ ለጠ/ሚ አብይ አህመድ ትሸልማለች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ካምፓላ ገብተዋል።

በነገው እለትም የኡጋንዳ መንግስት ለአፍሪካ ነጻነት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሀገራት የምታበረክተውን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ይሸለማሉ።

ከዚህ ቀደም ኡጋንዳ ለኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዚዳንት ትዮዶሮ ኦቢያንግ ተመሳሳይ ሽልማት ሸልማለች።

የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ እንደተናገሩት “ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በሀገራችን በመገኘታቸው ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል። በሁለት ቀናት ቆይታቸው ከፕሬዚዳንቱ ጋር በበርካታ የጋራ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ” በማለት ለጋዘጠኞች ተናግረዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply