ኢትዮጵያና ኢኳዶር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢትዮጵያና ኢኳዶር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ሀገራት ስመምነቱን የተፈራረሙት በአሜሪካ ኒው ዮርክ እየተካሄደ ካለው 73ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባዔ ጎን ለጎን ነው።

ስምምነቱንም በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በኢኳደር በኩልም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴ ቫሌንሺያ ፈርመዋል።

በስምምነቱም የኢትዮጵያና ኢኳዶር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እና በሁለቱ ሀገራት መካከል የቪዛ አገልግሎት ማስጀመርን ያካትታል።

በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የፖለቲካ ምክክር ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply