ኢትዮጵያና ዛንዚባር በእድሜ ማጭበርበር ክስ በሴካፋ ቅጣት ተጣለባቸው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢትዮጵያና ዛንዚባር በእድሜ ማጭበርበር ክስ በሴካፋ ቅጣት ተጣለባቸው

ኢትዮጵያና ዛንዚባር ከ17 ዓመት በታች ባሉ ታዳጊዎች በሚደረግ የሴካፋ የእግር ኳስ ውድድር ላይ በእድሜ ማጭበርበር ተከሰው ቅጣት ተጣለባቸው፡፡

በብሩንዲ ከ17 ዓመት በታች ባሉ የሴካፋ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ሻምፒዮና እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በውድድሩ ከተቀመጠው ገደብ በላይ እድሜያቸው የገፋ ሶስት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከሻምፒዮናው እንዲሰናበቱ ተደርጓል፡፡

የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር /ሴካፋ/ ፊፋ በውድድሩ ለተጫዋቾቹ ያወጣውን ገንዘብ ለማስመለስ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ የ5 ሺህ ዶላር የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ሶማሊያን በማሸነፍ ያገኘችው 3 ነጥብ የተቀንሶባት ሲሆን ሶማሊያም አሁን ሶስት ነጥብ እና ሶስት የግብ ክፍያ አላት ማለት ነው፡፡

በተቃራኒው ኢትዮጵያ ደግሞ ምንም ነጥብ ሳይኖራት የ3 ግብ እዳ አለባት፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታውን ከኬንያ ጋር እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

በተመሳሳይ ከሱዳን ጋር በነበራት ግጥሚያ ከውድድሩ የእድሜ ጣሪያ በላይ የሆኑ 12 ተጫዋቾችን ባሰለፈችው ዛንዚባር ላይም በቀጠናው ከማንኛውም የእግር ኳስ ተሳትፎዋ ታግዳለች፡፡

ሴካፋ ሀገሪቱ ላይ 15 ሺህ ዶላር ቅጣት የጣለ ሲሆን የቅጣቱ ክፍያ ሲፈጸም የተጣለው እገዳ እንደሚነሳ ኦል አፍሪካ ድረ-ገጽ ካፒታል ኤፍኤምን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፡ ኦል አፍሪካ፤ ካፒታል ኤፍኤም

Share.

About Author

Leave A Reply