ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሰብ እስከ አዲስ አበባ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ለመዘርጋት አቅደዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሪም አል ሀሺሚን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህ ወቅትም ሀገራቱ ከዚህ ቀደም የደረሷቸውን የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ወደ ተጨባጭ ስራ ለማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይተዋል።

በሀገራቱ መካከል የተገቡ ስምምነቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር በባለሙያዎችና በቴክኒክ ደረጃ ጥናት እየተካሄደ እንደሆነ ተነስቷል።

በዚህ ውይይት በተለይ የሪል እስቴት እና ሪዞርት ግንባታዎችን በፍጥነት ለመጀመር ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ታውቋል።

በተጨማሪም ከአሰብ እስከ አዲስ አበባ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ለመዘርጋት ሀገራቱ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን፥ ይህንም ወደ ተግባር ለመቀየር ጥናት ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ከውይይቱ በኋላ ሚኒስትሯ ሪም አል ሀሽሚ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ አሟጣ ለመጠቀም ትፈልጋለች ብለዋል።

በአሁን ወቅትም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለዚህም መልካም አጋጣሚ አንደሆነ ጠቁመዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply