ኢትዮጵያዊ ግብር በቴዲ አፍሮ መኖሪያ ቤት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞና ዘርፈ ብዙዋ ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ከረጅም አመታት የውጭ ሃገር ቆይታ በኋላ በቅርቡ ወደ ሃገራቸው የገቡትን ወዳጆቹንና በሃገር ውስጥ ላሉ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በመኖሪያ ቤታቸው ግብር አግብተው ነበር።
የአባቶቹ ልጅ ቴዲ በታላቅ የኢትዮጵያዊነት እንግዳ አቀባበል ስርዓትና ባህል በጠበቀ መልኩ ባዘጋጀው በዚህ ልዩ የእራት መርሃ ግብር ላይ የታደሙ ወዳጆቹ የተደሰቱበት፣ የተዝናኑበት፣ በሳቅና ቁም ነገር የታጀበ አስደሳች ምሽት እንደ ነበር ገልፀውልኛል።

የማስታወቂያው አባት ውብሸት ወርቃለማሁ
ሁለገቧ አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጇ ከነ ልጇ
አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ
ተወዳጁ አርቲስት ተስፋዬ ገብረሃና
የፀሃይ አሳታሚ ባለቤትና መስራች ኤልያስ ወንድሙ
የዘሃበሻ ጋዜጣና ድረገፅ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሄኖክ ደግፉ
የኢትዮ ፎረም ድረገፁ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ
የፊልም ባለሙያውና የበጎ ተግባር አጋፋሪው ያሬድ ሹመቴ
የአንጋፋው ጋዜጠኛ ከፍያለው ማሞ ልጅ ሚሚ ከፍያለው
እንዲሁም የቴዲ አፍሮ የቅርብ ጓደኞች ታድመው የነበሩ ሲሆን፤
የቴዲ አፍሮ ወላጅ እናት የመድረኳ ንግስት ጥላዬ አራጋው፣
አንጋፋው ጋዜጠኛና የቴዲ አፍሮ ማናጀር ጌታቸው ማንጉዳይ በመስተንግዶው በአጋፋሪነት የሃረሩን ሰንጋ ቁርጥ ስጋ ዳቢት ከሻና፣ ጎዲን ከጭቅና ሲያስቆርጡና በልዩ የጎጃም ማር የተጣለውን ጠጅ ሲያሳልፉ አምሽተዋል።

ቴዲ አፍሮ በዘፈኖቹ ብቻ ሳይሆን በግብሩም ኢትዮጵያዊ መሆኑንም በመኖሪያ ቤቱ ባሉት ቁሳቁሶችና መፃሕፍትም ጭምር አስጎብኝቷቸዋል።

(ምንጭ ጴጥሮስ አሸናፊ)

Share.

About Author

Leave A Reply