ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም የማዛወሩን ሀሳብ ሰረዘች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አሜሪካ ባለፈው ወር ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ማዛወሯን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ኤምባሲያቸውን እያዛወሩ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መንግስትም ተመሳሳይ ዝግጂት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ ጉዳዩን ለማዘግየት መወሰኑ ተዘግቧል።

በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ የህግ አማካሪ ትናንት ሰኞ ለቻናል 10 በሰጡት ማብራሪያ “የኢትዮጵያን ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሩን ላልተወሰነ ጊዜ አቁመነዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሀሳቡን ሊቀይር የቻለውም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ንብረት በሆነው ህንጻ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መነኮሳትን የእስራኤል ወታደሮች በሀይል አስወጥተዋል በሚል ነው።

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተገነባ ህንጻ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ መነኮሳት “ይህ የእናንተ አይደለም” በማለት ከህግ አግባብ ውጪ አስወጥተዋቸዋል በሚል ነው ኤምባሲው ዝውውሩን ያቆመው።

Share.

About Author

Leave A Reply