ኢትዮጵያ “ዩጎስላቪያ” አይደለችም – ምርጫው ልማት ወይንም እልቂት ነው (አክሎግ ቢራራ (ዶር)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ በፊት አይቶትና ሰምቶት የማያውቀውን የሰብአዊ መብት መከበር፤ በነጻ የመናገርና የመጻፍ፤ መንግሥትን የመተቸት፤ እንደልብ የመንቀሳቀስና የመደራጀት፤ የመሰብሰብ፤ ከአገር የመውጣትና የመግባት መብቶችን ተቀዳጅቷል። ችግሮችን በጋራና በሰላም የመፍታትና የኢትዮጵያን ጥልቀት ያለው የኋላ ቀርነትና የድህነት ሰቆቃ ለመቅረፍ እድሉ ከፍ ብሏል። ኢትዮጵያን ካስቀደምና ከዘውግ በላይ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብትና ደህንነት ለማሰብና ለመስራት ከቻልን፤

ኢትዮጵያ በአስርት ዓመታት ረሃብን፤ ፍጹም ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ ትችላለች፤
ኢትዮጵያ ዩጎስላቭያን አትሆንም። ይህን ማድረግ ግን ቀላል አይሆንም፤ ብዙ አስመሳዮችና ጠባብ ብሄርተኞች የከበቡት መንግሥት ሆኗል።
መጀመሪያ የፖለቲካውን ችግር በጋራ፤ በቅንነትና በድፍረት ለመፈታት ፈቃደኛ መሆን አለብን። የመንግሥቱ መሪዎች ደፋር መሆን አለባቸው።

የኢትዮጵያን ረጅም፤ የሚያኮራና የጋራ ታሪክ ሂደት፤ የዘውግን ጠባብ ብሄርተኝነት አደጋነት፤ አድካሚነትና አፍራሽነት፤ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መለያ ወይንም የኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት አስፈላጊነትና ወሳኝነት፤ ጦርነትን ወደ ጎን ትቶ ኋላ ቀርነትንና ድህነትን የመቅረፍና የማሸነፍ ወሳኝነትን ወዘተ እሴቶች በሚመለከት ብዙ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። ይህች የብዙ ሽህዎች ዓመታት ታሪክ ያላት አገር በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገና ስለ አገር ግንባታ (Nation-building) ጥናት፤ ምርምርና ውይይት ታደርጋለች። ለማስታወስ፤ እኛ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን መናገር፤ መጻፍና መተቻቸት እንወዳለን። በጋራ እሴቶች መስማማት ግን አንችልም። “Quo Vadis Ethiopia (ኢትዮጵያ ወደ የት እየሄደች ነው?”) የሚለውን ጥያቄ ያልፈተሸ ምሁር ወይንም ስብስብ የለም። ይህ ባለፉት አምሳ ዓመታት ሲፈተሽ የቆየ ጥያቄ ሁሉም ምሁራን፤ ልሂቃን፤ የፖለቲካ ስብስቦች፤ መሪዎች የሚጋሩት መልስ አለማግኘቱ ይህች ታላቅ አገር አሁንም በራሷ ዜጎች እየተጎዳች መሆኑን ያሳያል። አገሩን የማያከብርና በማያሻማ ደረጃ የማይቀበል ዜጋ ወይንም ቡድን ሕዝብን ይወዳል፤ ለፍትህ ቆሟል ለማለት አይቻልም፤ የሚወደው ራሱንና የራሱን ዝና ነው። የሚያገለግለው የራሱንና የቡድኑን ጥቅም ነው።

የችግሩ መንስኤ ኢትዮጵያ ወይንም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደሉም። ኢትዮጵያን እንደ ችግር የምናቀርባትና የምነወያይባት እኛው ነን። የቻይና ሕዝብ ቻይናን፤ የአሜሪካ ሕዝብ አሜሪካን፤ የራሽያ ሕዝብ ራሽያን፤ የኢራን ሕዝብ ኢራንን፤ የግብጽ ሕዝብ ግብጽን ወዘተ እንደ ችግር አያይም። የሰለጠነውና አገሩን ዘመናዊ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ የዓለም ሕዝብ፤ የፖለቲካውንና የፓርቲውን ልዩነት ከአገሩ ዘላቂነትና ብሄራዊ ጥቅም ይለያል። አገር እንደ ችግር አይታይም፤ ችግሩ የፖለቲካ ሥልጣን ፈላጊዎች ናቸው ። ዓለም ያደነቃትን አገር ኢትዮጵያን ዛሬም የምናዋርዳት፤ ሌላው ቀርቶ አሁንም በስሟ ፓርቲዎችንና ተቋማትን ለመሰየም የምንቸገረው፤ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት፤ የአገሪቱ አምባሳደሮች አይን ባወጣ ደረጃ የኢትዮጵያን ዘላቂ የንግድ፤ የመዋእለ ንዋይ ፈሰስ አስፈላጊነት ጥቅም፤ የሁሉም ዜጎቿ የመከበርና የመገልገል መብት፤ የአገራችን የመከበርና የዜግነት መለያችን መሆኑን የማስተጋባትን ግዴታቸውን ወደጎን ትተው ኤምባሲዎችን የራሳቸው ዘውግ አባላት መሰብሰቢያና መገልገያ ማድረጋቸው ምን ያህል ይህችን ታላቅ አገር ዝቅ እንዳደረግናት ያሳያሉ። የኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ የመላው ሕዝቧ እድገትና በሁለመናዋ ተሳታፊነት የህልውና ጥያቄ መሆኑን “ኢትዮጵያ ወደ የት እየሄደች ነው” በሚሉት ስብሰባዎች ስነወያይባቸው ቆይተናል።

ዛሬ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልጉት ተግባር እንጅ ዲስኲር አይደለም። ኢትዮጵያ ፍትሃዊና አስተማማኝ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመመስረት የምትችለው የሕግ የበላይነት፤ እውነተኛ እኩልነት፤ በዜግነት መብት የተመሰረተ፤ ብሄርና ቋንቋ ተኮሩን ሕገ መንግሥት የሚተካ ሌላ ሕዝብ ተወያይቶና ተስማምቶ የተቀበለው ሕገ መንግሥት ስኬታማ ሲሆን ነው። ችግሩ ሕገ መንግሥቱ አይደለም፤ አፈጻጸም ነው የሚለውን ብሂል አልቀበልም። በዜጎች መብት ላይ ያልተመሰረተ፤ ሕብረ-ብሄራዊነትን ያዳከመ ሕገ መንግሥት እንዴት አግባብ አለው ለማለት ይቻላል?

ያለውን የአንድ ፓርቲ ስርዓት ለማጠናከርና የጥቂቶችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት መልሶ እንዲያንሰራራ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ካልተፈለገ በስተቀር፤ በአሁኑ ወቅት፤ “ሕገ መንግሥቱ ይከበር፤ ምርጫ ለይስሙላ ይካሄድ” ማለቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል። ምክንያቱም፤ የብሄር ጥላቻው ስር እንደሰደደ ነው። ቅደመ ሁኔታዎች አልተመቻቹም። ከአዲስ አበባና ሌሎች ጥቂት ቦታዎች ውጭ ሰላምና እርጋታ፤ የሕግ የበላይነት፤ አስተማማኝ ኑሮ ወዘተ የለም። ከፍተኛ ሌቦችና ነፍሰ ገዳዮች በሃላፊነት ለፍርድ አልቀረቡም።

ለምሳሌ፤ ባለፈው ሳምንት፤ በ February 6, 2019 የመጀመሪያ ቀናት ብቻ በደምቢያ ወረዳ ጎንደር ጦርነት ተካሂዶ ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ዜጎች ህይወት አልፏል፤ ብዙ ኃብት ወድሟል። ዶቸ ቬላ እንዳታወቀው ከሆነ የችግሩ መነሻ በጭልጋ ወረዳ በሚኖሩ “የዐማራና የቅማንት” ወንድማማች ሕዝቦች መካከል በተከሰተ ልዩነት ነው። ይህን ልዩነት በተከትጋታይ እሳት እየጫሩ ያባባሱት ህወሓቶች መሆናቸው የሚከራክር አይመስለኝም። ህወሓት ሥልጣን ከመያዙ በፊት በዚህና በሌሎች የጎንደር አካባቢዎች የተጨፈጨፈው ሕዝብ ብዛት በቅጡ ባይታወቅም፤ በብዙ ሽህዎች ይገመታል። ዛሬም እንደ ትላንቱ፤ የህወሓቶች ዐላማ ጎንደርን ማውደምም ባይችሉ በዘረፉት ኃብትና በገዙት መሳሪያ ጎንደርንና ጎንደሬውን ማድቀቅና ማዳከም ነው። ይህ ሁኔታ ከቀጠለና ከተስፋፋ የሚካሄደው ጦርነት በመላው ዐማራ ሕዝብ ላይ እንደሚሆን መጠራጠር የለብንም። ችግሩ የጎንደሬው ብቻ አይደለም።

ንባቦን ይህን ሊንክ ተጭነው ይቀጥሉ

Share.

About Author

Leave A Reply