ኤርትራ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሆኑ እስረኞችን ፈታች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኤርትራ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሆኑ እስረኞችን ፈታች

የኤርትራ መንግስት ለአመታት አስሮ ያቆያቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን መልቀቁ ተዘግቧል።

እ.ኤ.አ. 2002 የሀገሪቱ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ የኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ የሉተራን እምነት፣ እና የሱኒ እስላም እምነቶች ብቻ በመፍቀድ ከዚህ ውጪ ያሉትን ግን በህግ ማገዱ ይታወሳል።

መንግስት ለዚህ እንደ መነሻ የወሰደው ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገው የድንበር ግጭት ወቅት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮቿን በወታደርነት እንዳያገለግሉ በመስበኳ እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል።

ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ ውስጥ በህገ ወጥ እምነት ማራመድ በሚል በርካታ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን ማሰሩ ይታወቃል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply