ኤርትራ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ከሰሰች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢትዮጵያ ክሱን “የኤርትራ መንግስት የተለመደ አስቂኝ ድራማ ነው” ስትል ውድቅ አድርጋዋለች

ኢትዮጵያና ሱዳን ለ27 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየውን የፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቄን መንግስት ለመጣል መክረዋል ስትል አስታወቀች።

የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫው እንደጠቆመው፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ እና የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በሱዳን ካርቱም ባደረጉት ውይይት የኤርትራን መንግስት ለመጣል የታጠቁ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎችን ለመርዳት ተስማምተዋል፡፡

የኤርትራ አማጽያን ኃይሎች በተለይ ከኳታር መንግስት በሚያገኙት የገንዘብና የቁሳቁስ እገዛ በኤርትራ መንግስት ላይ እያሴሩ ነው ሲል መግለጫው አክሏል።

የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያንና ሱዳንን ሲከስ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። በተመሳሳይ ከዚህ ቀደምም የኳታር መንግስት ኤርትራን ለማጥቃት ተዋጊ ጄትና በርካታ የጦር መሳሪያ ለሱዳን መንግስት ስጥታለች ሲል መክሰሱ ይታወቃል፡፡

በዚህ የኤርትራ መንግስት መግለጫ ዙሪያ አስተያየቱን የተጠየቀው የአፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክሱን እንደማይቀበለው በመግለጽ የኤርትራ መግስትን ክስ ውድቅ አድርጎታል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ምላሽም፤ “የአሁኑ ክስ የኤርትራ መንግስት በየጊዜው የሚከውነው መቋጫ የሌለው አስቂኝ ድራማ (ኮሜዲ) ተከታይ ክፍል ነው” ሲሉ መግለጫውን ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጸዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply