እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ለቅጣት ወደ ዝዋይ ተወስደዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(ጌታቸው ሽፈራው)

የቂሊንጦ እስር ቤት በትህነግ ታጋዮች የተሞላ ነው። አሰፋ ኪዳነ ዋና ኃላፊ ነው። እነ ካዕሱ፣ ጉዕሽ፣ ተወልደ፣ ገብረማርያም ናቸው አዛዦቹ።

እነዚህ የትህነግ ታጋዮች ከፍርድ ቤቱ በላይ በራሳቸው ፍርድ ያምናሉ። እሱ ደግሞ ቅጣት ነው። ለአማራና ኦሮሞ ተወላጆች ያላቸው ጥላቻ የበረታ ነው።

“ሽብር” ተብሎ የተከሰሰን ከፍርድ ቤት በፊት አሸባሪ ብለው ይበይኑበታል። ፍርድ ቤት ላይ የተናገረ ሲመለስ ግርፋት ይጠብቀዋል። እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ (38ቱ ተከሳሾች) ሚያዝያ 30 ችሎታቸው ተቋርጧል። ፍርድ ቤት ምንም አላላቸውም የእነ አሰፋ ኪዳነ ተቋም ግን ማታ ጨለማ ቤት አስገባቸው፣ ተገረፉ።

ዛሬ ደግሞ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ ፍቅረማርያም አስማማውን ጨምሮ 16 ተከሳሾች ለቅጣት ወደ ዝዋይ እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።

በ2009 ዓም ሀምሌ ወር አግባው ሰጠኝን ጨምሮ 22 እስረኞች ወደ ዝዋይ ተወስደው ተገርፈዋል። አቧራ ላይ ራቁታቸውን እያንከባለሉ፣ ውሃ እየደፉ ገርፈዋቸዋል። ዛሬም እነ ማስረሻ የተወሰዱት ወደዛ ጭካኔ ቤት ነው!

Share.

About Author

Leave A Reply